በመክፈት ላይ

ጥንተ ስቅለቱ ለመድኃኔዓለም

ጥንተ ስቅለቱ ለመድኃኔዓለም

በዕለቱ የሚነበቡት መልዕክታት

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች:- ም. 12 ቊ. 2-18 / St Paul’s letter to the Hebrews:- ch. 12 nu. 2-18

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች:- ም. 12 ቊ. 2-18 </br> St Paul’s letter to the Hebrews:- ch. 12 nu. 2-18

2፤ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።

3፤ በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።

4፤ ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤

5-6፤ እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፦ “ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡” ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።

7፤ ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

8፤ ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።

9፤ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?

10፤ እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።

11፤ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።

12፤ ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤

13፤ ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።

14፤ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።

15፤ የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥

16፤ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።

17፤ ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።

18፤ ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤

 St Paul’s letter to the Hebrews:- ch. 12 nu. 2-18

2. Looking unto Jesus the author and finisher of our faith; who for the joy that was set before him endured the cross, despising the shame, and is set down at the right hand of the throne of God.

3. For consider him that endured such contradiction of sinners against himself, lest ye be wearied and faint in your minds.

4. Ye have not yet resisted unto blood, striving against sin.

5. And ye have forgotten the exhortation which speaketh unto you as unto children, My son, despise not thou the chastening of the Lord, nor faint when thou art rebuked of him:

6. For whom the Lord loveth he chasteneth, and scourgeth every son whom he receiveth.

7. If ye endure chastening, God dealeth with you as with sons; for what son is he whom the father chasteneth not?

8. But if ye be without chastisement, whereof all are partakers, then are ye bastards, and not sons.

9. Furthermore we have had fathers of our flesh which corrected us, and we gave them reverence: shall we not much rather be in subjection unto the Father of spirits, and live?

10. For they verily for a few days chastened us after their own pleasure; but he for our profit, that we might be partakers of his holiness.

11. Now no chastening for the present seemeth to be joyous, but grievous: nevertheless afterward it yieldeth the peaceable fruit of righteousness unto them which are exercised thereby.

12. Wherefore lift up the hands which hang down, and the feeble knees;

13. And make straight paths for your feet, lest that which is lame be turned out of the way; but let it rather be healed.

14. Follow peace with all men, and holiness, without which no man shall see the Lord:

15. Looking diligently lest any man fail of the grace of God; lest any root of bitterness springing up trouble you, and thereby many be defiled;

16. Lest there be any fornicator, or profane person, as Esau, who for one morsel of meat sold his birthright.

17. For ye know how that afterward, when he would have inherited the blessing, he was rejected: for he found no place of repentance, though he sought it carefully with tears.

18. For ye are not come unto the mount that might be touched, and that burned with fire, nor unto blackness, and darkness, and tempest,

አንደኛው የጴጥሮስ መልዕክት:- ም. 3 ቊ. 15-20 / St Peter’s First letter:- ch. 3 nu. 15-20

አንደኛው የጴጥሮስ መልዕክት:- ም. 3 ቊ. 15-20

15፤ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።

16፤ በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።

17፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና።

18፤ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥

19፤ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤

20፤ ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።

 St Peter’s First letter:- ch. 3 nu. 15-20

15. But sanctify the Lord God in your hearts: and be ready always to give an answer to every man that asketh you a reason of the hope that is in you with meekness and fear:

16. Having a good conscience; that, whereas they speak evil of you, as of evildoers, they may be ashamed that falsely accuse your good conversation in Christ.

17. For it is better, if the will of God be so, that ye suffer for well doing, than for evil doing.

18. For Christ also hath once suffered for sins, the just for the unjust, that he might bring us to God, being put to death in the flesh, but quickened by the Spirit:

19. By which also he went and preached unto the spirits in prison;

20. Which sometime were disobedient, when once the longsuffering of God waited in the days of Noah, while the ark was a preparing, wherein few, that is, eight souls were saved by water.

የሐዋርያት ሥራ:- ም. 10 ቊ. 30-40 / Acts of The Apostles:- ch. 10 nu. 30-40

የሐዋርያት ሥራ:- ም. 10 ቊ. 30-40

30፤ ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው፦ “በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና፦

31፤ ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።

32፤ እንግዲህ ወደ ኢዮጴ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስጠራ፤ እርሱ በቍርበት ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ እንግድነት ተቀምጦአል፡’ አለኝ።

33፤ “ስለዚህ ያን ጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፥ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”

34-35፤ ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደ ሆነ በእውነት አስተዋልሁ።

36፤ የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ።

37፤ ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ ሁሉ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ።

38፤ እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

39፤ እኛም በአይሁድ አገርና በኢየሩሳሌም ባደረገው ነገር ሁሉ ምስክሮች ነን፤ እርሱንም በእንጨት ላይ ሰቅለው ገደሉት።

40፤ እርሱን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤
 Acts of The Apostles:- ch. 10 nu. 30-40

30. And Cornelius said, Four days ago I was fasting until this hour; and at the ninth hour I prayed in my house, and, behold, a man stood before me in bright clothing,

31. And said, Cornelius, thy prayer is heard, and thine alms are had in remembrance in the sight of God.

32. Send therefore to Joppa, and call hither Simon, whose surname is Peter; he is lodged in the house of one Simon a tanner by the sea side: who, when he cometh, shall speak unto thee.

33. Immediately therefore I sent to thee; and thou hast well done that thou art come. Now therefore are we all here present before God, to hear all things that are commanded thee of God.

34. Then Peter opened his mouth, and said, Of a truth I perceive that God is no respecter of persons:

35. But in every nation he that feareth him, and worketh righteousness, is accepted with him.

36. The word which God sent unto the children of Israel, preaching peace by Jesus Christ: (he is Lord of all:)

37. That word, I say, ye know, which was published throughout all Judaea, and began from Galilee, after the baptism which John preached;

38. How God anointed Jesus of Nazareth with the Holy Ghost and with power: who went about doing good, and healing all that were oppressed of the devil; for God was with him.

39. And we are witnesses of all things which he did both in the land of the Jews, and in Jerusalem; whom they slew and hanged on a tree:

40. Him God raised up the third day, and shewed him openly;

ምስባክ

እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም፤
ወገብረ መድኀኒተ በማእከለ ምድር።
አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኀይልከ።
መዝሙር:- ፸፫: ፲፪-፲፫

እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥
በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።
አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት።
መዝሙር:- 74:12-13

For God is my King of old,
working salvation in the midst of the earth.
Thou didst divide the sea by thy strength.
Psalms:- 74:12-13

ወንጌል / Gospel

ማቴዎስ:- ም. ፳፯(27) ቊ. ፩(1)-፶፭(55) / Mathew :- ch. 27 nu. 1-55

ማቴዎስ:- ም. ፳፯(27) ቊ. ፩(1)-፶፭(55)

1፤ ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤

2፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

3፤ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦

4፤ “ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፡” አለ። እነርሱ ግን፦ “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፡” አሉ።

5፤ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።

6፤ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው፦ “የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም፡” አሉ።

7፤ ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።

8፤ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።

9፤ በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው፦ “ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥

10፤ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት፥” የሚል ተፈጸመ።

11፤ ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም፦ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም አለው፦ “አንተ አልህ።”

12፤ የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም።

13፤ በዚያን ጊዜ ጲላጦስ፦ “ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን?” አለው።

14፤ ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም።

15፤ በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው።

16፤ በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው።

17፤ እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ፦ “በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው፤

18፤ በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።

19፤ እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፡” ብላ ላከችበት።

20፤ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ።

21፤ ገዢውም መልሶ፦ “ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም፦ “በርባንን፡” አሉ።

22፤ ጲላጦስ፦ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም፦ “ይሰቀል፡” አሉ።

23፤ ገዢውም፦ “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን፦ “ይሰቀል” እያሉ ጩኸት አበዙ።

24፤ ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ፦ “እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ” ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።

25፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው፦ ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፡” አሉ።

26፤ በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።

27፤ በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።

28፤ ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥

29፤ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው፦ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ ዘበቱበት፤

30፤ ተፉበትም፡ መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።

31፤ ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

32፤ ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።

33፤ ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥

34፤ በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።

35፤ ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥

36፤ በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።

37፤ ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።

38፤ በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዶች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ።

39፤ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና፦

40፤ “ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ፡” አሉት።

41፤ እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ፦

42፤ “ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን።

43፤ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው።”

44፤ ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዶች ደግሞ ያንኑ እያሉ ይነቅፉት ነበር።

45፤ ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።

46፤ በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።

47፤ በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው፦ “ይህስ ኤልያስን ይጠራል፡” አሉ።

48፤ ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው።

49፤ ሌሎቹ ግን፦ “ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ፡” አሉ።

50፤ ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።

51፤ እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤

52፤ መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤

53፤ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።

54፤ የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፡” ብለው እጅግ ፈሩ።

55፤ ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤

Mathew :- ch. 27 nu. 1-55

1. When the morning was come, all the chief priests and elders of the people took counsel against Jesus to put him to death:

2. And when they had bound him, they led him away, and delivered him to Pontius Pilate the governor.

3. Then Judas, which had betrayed him, when he saw that he was condemned, repented himself, and brought again the thirty pieces of silver to the chief priests and elders,

4. Saying, I have sinned in that I have betrayed the innocent blood. And they said, What is that to us? see thou to that.

5. And he cast down the pieces of silver in the temple, and departed, and went and hanged himself.

6. And the chief priests took the silver pieces, and said, It is not lawful for to put them into the treasury, because it is the price of blood.

7. And they took counsel, and bought with them the potter’s field, to bury strangers in.

8. Wherefore that field was called, The field of blood, unto this day.

9. Then was fulfilled that which was spoken by Jeremy the prophet, saying, And they took the thirty pieces of silver, the price of him that was valued, whom they of the children of Israel did value;

10. And gave them for the potter’s field, as the Lord appointed me.

11. And Jesus stood before the governor: and the governor asked him, saying, Art thou the King of the Jews? And Jesus said unto him, Thou sayest.

12. And when he was accused of the chief priests and elders, he answered nothing.

13. Then said Pilate unto him, Hearest thou not how many things they witness against thee?

14. And he answered him to never a word; insomuch that the governor marvelled greatly.

15. Now at that feast the governor was wont to release unto the people a prisoner, whom they would.

16. And they had then a notable prisoner, called Barabbas.

17. Therefore when they were gathered together, Pilate said unto them, Whom will ye that I release unto you? Barabbas, or Jesus which is called Christ?

18. For he knew that for envy they had delivered him.

19. When he was set down on the judgment seat, his wife sent unto him, saying, Have thou nothing to do with that just man: for I have suffered many things this day in a dream because of him.

20. But the chief priests and elders persuaded the multitude that they should ask Barabbas, and destroy Jesus.

21. The governor answered and said unto them, Whether of the twain will ye that I release unto you? They said, Barabbas.

22. Pilate saith unto them, What shall I do then with Jesus which is called Christ? They all say unto him, Let him be crucified.

23. And the governor said, Why, what evil hath he done? But they cried out the more, saying, Let him be crucified.

24. When Pilate saw that he could prevail nothing, but that rather a tumult was made, he took water, and washed his hands before the multitude, saying, I am innocent of the blood of this just person: see ye to it.

25. Then answered all the people, and said, His blood be on us, and on our children.

26. Then released he Barabbas unto them: and when he had scourged Jesus, he delivered him to be crucified.

27. Then the soldiers of the governor took Jesus into the common hall, and gathered unto him the whole band of soldiers.

28. And they stripped him, and put on him a scarlet robe.

29. And when they had platted a crown of thorns, they put it upon his head, and a reed in his right hand: and they bowed the knee before him, and mocked him, saying, Hail, King of the Jews!

30. And they spit upon him, and took the reed, and smote him on the head.

31. And after that they had mocked him, they took the robe off from him, and put his own raiment on him, and led him away to crucify him.

32. And as they came out, they found a man of Cyrene, Simon by name: him they compelled to bear his cross.

33. And when they were come unto a place called Golgotha, that is to say, a place of a skull,

34. They gave him vinegar to drink mingled with gall: and when he had tasted thereof, he would not drink.

35. And they crucified him, and parted his garments, casting lots: that it might be fulfilled which was spoken by the prophet, They parted my garments among them, and upon my vesture did they cast lots.

36. And sitting down they watched him there;

37. And set up over his head his accusation written, THIS IS JESUS THE KING OF THE JEWS.

38. Then were there two thieves crucified with him, one on the right hand, and another on the left.

39. And they that passed by reviled him, wagging their heads,

40. And saying, Thou that destroyest the temple, and buildest it in three days, save thyself. If thou be the Son of God, come down from the cross.

41. Likewise also the chief priests mocking him, with the scribes and elders, said,

42. He saved others; himself he cannot save. If he be the King of Israel, let him now come down from the cross, and we will believe him.

43. He trusted in God; let him deliver him now, if he will have him: for he said, I am the Son of God.

44. The thieves also, which were crucified with him, cast the same in his teeth.

45. Now from the sixth hour there was darkness over all the land unto the ninth hour.

46. And about the ninth hour Jesus cried with a loud voice, saying, Eli, Eli, lama sabachthani? that is to say, My God, my God, why hast thou forsaken me?

47. Some of them that stood there, when they heard that, said, This man calleth for Elias.

48. And straightway one of them ran, and took a spunge, and filled it with vinegar, and put it on a reed, and gave him to drink.

49. The rest said, Let be, let us see whether Elias will come to save him.

50. Jesus, when he had cried again with a loud voice, yielded up the ghost.

51. And, behold, the veil of the temple was rent in twain from the top to the bottom; and the earth did quake, and the rocks rent;

52. And the graves were opened; and many bodies of the saints which slept arose,

53. And came out of the graves after his resurrection, and went into the holy city, and appeared unto many.

54. Now when the centurion, and they that were with him, watching Jesus, saw the earthquake, and those things that were done, they feared greatly, saying, Truly this was the Son of God.

55. And many women were there beholding afar off, which followed Jesus from Galilee, ministering unto him:

ቅዳሴ / Liturgy

ቅዳሴ:- ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ
Anaphora:- St John Chrysostom

ጥንተ ስቅለት
መጋቢት 27 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን ዐርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል፡፡መጋቢት 27 ቀን በዐቢይ ጾም ስለሚውልና በወቅቱም ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች ።

“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።” ዮሐ 3፡14

መጋቢት 27 የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትና ዓለምን ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ያዳነበት የጥንተ ስቅለት መታሰቢያ ነው።

መልካም በዓል!

ለሌሎች ያጋሩ

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

በደብራችን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ።

በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት ኅዳር 21/2018 ዓ/ም በለንደን ጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀብለዋል።

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

ዜና ቤተክርስቲያን

በዛሬው ዕለት በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንየመጭውን የጻድቁ አባታችንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት ለሚደረገው ዝግጅት በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ጥረት የህንጻ ግዢ የገቢ አሰባሳቢክፍሉ በደብሩ ያሉትን የአገልግሎት ክፍሎች በጋራ ሊያሳካ ስለሚችለው ውይይት አድርጏል ለዚሁም ይረዳው ዘንድ በዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቅም ስልጠና ተሰጥቷል::

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

ዜና ቤተክርስቲያን

በትናንትናው ዕለት ማለትም በ17/12/2017 ዓም (August 23/2025) በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አንድ አዲስ ነገር ተፈፅሟል ይኸውም ጀማል የተባለ ከእስልምና ወደ ክርስትና በመምጣት መስረታዊ የክርስትና ትምህርቱን በተገቢ መንገድ አጠናቅቆ የሥላሴ ልጅነቱን አግኝቷል ትምህርቱንም የሰጠው ዲያቆን ዘማርያም ሲሆን በደብራችንም ተጨማሪ ክትትል በማድረግ እነሆ ተከናውኗል እግዚአብሔር ይመስገን::