የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት – ኒቆዲሞስ/Nicodemus
በዕለቱ የሚነበቡት መልዕክታት
የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች:- ም. 7 ቊ. 1-12 / St Paul’s letter to Romans:- ch. 7 nu. 1-12
የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች:- ም. 7 ቊ. 1-12
1፤ ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን?
2፤ ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።
3፤ ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም።
4፤ እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ።
5፤ በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤
6፤ አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።
7፤ እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር፤ ሕጉ፦ “አትመኝ፡” ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና።
8፤ ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና።
9፤ እኔም ዱሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤
10፤ ለሕይወትም የተሰጠችውን ትእዛዝ እርስዋን ለሞት ሆና አገኘኋት፤
11፤ ኃጢአት ምክንያት አግኝቶ በትእዛዝ አታሎኛልና በእርስዋም ገድሎኛል።
12፤ ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት።
St Paul’s letter to Romans:- ch. 7 nu. 1-12
1. Know ye not, brethren, (for I speak to them that know the law,) how that the law hath dominion over a man as long as he liveth?
2. For the woman which hath an husband is bound by the law to her husband so long as he liveth; but if the husband be dead, she is loosed from the law of her husband.
3. So then if, while her husband liveth, she be married to another man, she shall be called an adulteress: but if her husband be dead, she is free from that law; so that she is no adulteress, though she be married to another man.
4. Wherefore, my brethren, ye also are become dead to the law by the body of Christ; that ye should be married to another, even to him who is raised from the dead, that we should bring forth fruit unto God.
5. For when we were in the flesh, the motions of sins, which were by the law, did work in our members to bring forth fruit unto death.
6. But now we are delivered from the law, that being dead wherein we were held; that we should serve in newness of spirit, and not in the oldness of the letter.
7. What shall we say then? Is the law sin? God forbid. Nay, I had not known sin, but by the law: for I had not known lust, except the law had said, Thou shalt not covet.
8. But sin, taking occasion by the commandment, wrought in me all manner of concupiscence. For without the law sin was dead.
9. For I was alive without the law once: but when the commandment came, sin revived, and I died.
10. And the commandment, which was ordained to life, I found to be unto death.
11. For sin, taking occasion by the commandment, deceived me, and by it slew me.
12. Wherefore the law is holy, and the commandment holy, and just, and good.
አንደኛው የዮሐንስ መልዕክት:- ም. 4 ቊ. 18-ፍ.ም / St John’s First letter:- ch. 4 nu. 18-end
አንደኛው የዮሐንስ መልዕክት:- ም. 4 ቊ. 18-ፍ.ም </br> St John’s First letter:- ch. 4 nu. 18-end
18፤ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
19፤ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
20፤ ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወዳለሁ፥” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፥ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
21፤ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።
St John’s First letter:- ch. 4 nu. 18-end
18. There is no fear in love; but perfect love casteth out fear: because fear hath torment. He that feareth is not made perfect in love.
19. We love him, because he first loved us.
20. If a man say, I love God, and hateth his brother, he is a liar: for he that loveth not his brother whom he hath seen, how can he love God whom he hath not seen?
21. And this commandment have we from him, That he who loveth God love his brother also.
የሐዋርያት ሥራ:- ም. 5 ቊ. 34-ፍ.ም / Acts of The Apostles:- ch. 5 nu. 34-end
የሐዋርያት ሥራ:- ም. 5 ቊ. 34-ፍ.ም </br> Acts of The Apostles:- ch. 5 nu. 34-end
34፤ ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥
35፤ እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
36፤ ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፦ እኔ ታላቅ ነኝ፡ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።
37፤ ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ፡ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።
38፤ አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤
39፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።”
40፤ ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።
41፤ እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤
42፤ ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።
Acts of The Apostles:- ch. 5 nu. 34-end
34. Then stood there up one in the council, a Pharisee, named Gamaliel, a doctor of the law, had in reputation among all the people, and commanded to put the apostles forth a little space;
35. And said unto them, Ye men of Israel, take heed to yourselves what ye intend to do as touching these men.
36. For before these days rose up Theudas, boasting himself to be somebody; to whom a number of men, about four hundred, joined themselves: who was slain; and all, as many as obeyed him, were scattered, and brought to nought.
37. After this man rose up Judas of Galilee in the days of the taxing, and drew away much people after him: he also perished; and all, even as many as obeyed him, were dispersed.
38. And now I say unto you, Refrain from these men, and let them alone: for if this counsel or this work be of men, it will come to nought:
39. But if it be of God, ye cannot overthrow it; lest haply ye be found even to fight against God.
40. And to him they agreed: and when they had called the apostles, and beaten them, they commanded that they should not speak in the name of Jesus, and let them go.
41. And they departed from the presence of the council, rejoicing that they were counted worthy to suffer shame for his name.
42. And daily in the temple, and in every house, they ceased not to teach and preach Jesus Christ.
ምስባክ
ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዐመፃ በላዕሌየ።
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው።
መዝሙር:- ፲፮: ፫-፬
ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤
ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው።
መዝሙር:- 17:3-4
Thou hast proved mine heart; thou hast visited me in the night;
thou hast tried me, and shalt find nothing;
I am purposed that my mouth shall not transgress.
Psalms:- 17:3
ወንጌል / Gospel
ዮሐንስ:- ም. ፫(3) ቊ. ፩(1)-፲፪(12) / John:- ch. 3 nu. 1-12
ዮሐንስ:- ም. ፫(3) ቊ. ፩(1)-፲፪(12)
1፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤
2፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና፡ መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡” አለው።
3፤ ኢየሱስም መልሶ፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም፡” አለው።
4፤ ኒቆዲሞስም፦ “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን?” አለው።
5፤ ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ “እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
6፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
7፤ ‘ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል’ ስላልሁህ አታድንቅ።
8፤ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።”
9፤ ኒቆዲሞስ መልሶ፦ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለው።
10፤ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?
11፤ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
12፤ ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
John:- ch. 3 nu. 1-12
1. There was a man of the Pharisees, named Nicodemus, a ruler of the Jews:
2. The same came to Jesus by night, and said unto him, Rabbi, we know that thou art a teacher come from God: for no man can do these miracles that thou doest, except God be with him.
3. Jesus answered and said unto him, Verily, verily, I say unto thee, Except a man be born again, he cannot see the kingdom of God.
4. Nicodemus saith unto him, How can a man be born when he is old? can he enter the second time into his mother’s womb, and be born?
5. Jesus answered, Verily, verily, I say unto thee, Except a man be born of water and of the Spirit, he cannot enter into the kingdom of God.
6. That which is born of the flesh is flesh; and that which is born of the Spirit is spirit.
7. Marvel not that I said unto thee, Ye must be born again.
8. The wind bloweth where it listeth, and thou hearest the sound thereof, but canst not tell whence it cometh, and whither it goeth: so is every one that is born of the Spirit.
9. Nicodemus answered and said unto him, How can these things be?
10. Jesus answered and said unto him, Art thou a master of Israel, and knowest not these things?
11. Verily, verily, I say unto thee, We speak that we do know, and testify that we have seen; and ye receive not our witness.
12. If I have told you earthly things, and ye believe not, how shall ye believe, if I tell you of heavenly things?
ቅዳሴ / Liturgy
ቅዳሴ ማርያም (እግዝእትነ)
ቅዱስ ያሬድ ንብ የማትቀስመው አበባ እንደሌላት ሁሉን ቀስማ ያማረ የጣፈጠ ማር እንድትሠራ እርሱም ሐዲሳትን ከብሉያት እያስማማ ለጀሮ የሚስማማ ኅሊናን የሚመስጥ ድንቅ ዜማ ባዘጋጀልን መሠረት የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ተብሎ ይጠራል፡፡ ሊቁ “ኒቆዲሞስ ስሙ ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ወይቤሎ በጽሚት ረቢ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጽአከ ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻአከ ከመ ትኩን መምሕረ ወበምጽአትከ አብራህከ ለነ ወሰላመ ጸጎከነ አንሥእ ኃይለከ ወነዓ አድኅነነ፤ አስቀድሞ በሌሊት ወደርሱ ይሔድ የነበረ ስሙ ኒቆድሞስ የሚባል ሰው በቀስታ “ሊቅ ሆይ ከአብ ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን” አለው። ኒቆዲሞስም ወደ እርሱ ሔደ፤ ረቢ ኢየሱስንም ሊቅ (አዋቂ) እንደሆንክ ለማስተማር ከአብ ዘንድም እንደመጣህ እኛ እናውቃለን፤ በምጽአትህም አበራህልን፤ ሰላምንም ሰጠኸን፤ ኃይልህን አንሳ፤ መጥተህም አድነን አለው” ይለናል። (ጾመ ድጓ)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር የአይሁድ አለቃ የሚሆን ኒቆዲሞስ የሚባል ሰው በሌሊት መጣ፤ ስለምን በሌሊት መጣ ቢሉ ከንቱ ውዳሴን ሽቶ አንተ የአይሁድ አለቃ ስትሆን እንዴት ትማራለህ እንዳይባል ሰው በማይመጣበት ከሰው ተለይቶ ሊማር ሽቶ በሌሊት መጣ። እንደዚሁም ምሁረ ኦሪት ነውና ምሥጢር ሊያደላድል ነው። በቀን ጌታን አምስት ገበያ ሕዝብ ይከተለው ስለነበር ለመጠየቅ አልተመቸውም ነበር፡፡ ጌታም በአእምሮ ያልጎለመሱ ሰዎችን ያስተምር ነበርና በምሳሌ እየመሰለ ያስተምራቸው ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ “እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?” እንዲል አጥንት ለመቆርጠም አልደረሱም ነበር። (፩ኛቆሮ.፫፥፩-፫) ኒቆዲሞስ ግን ምሁረ ኦሪት ነውና ጠንከር ያለ ትምህርት ሽቶ በሌሊት መጣ። በተጨማሪም የቀን ልቡና ባካና ነው ኅሊና ይሠረቃልና ክት ሊኅና ሽቶ በሌሊት ሊማር መጣ።
አባቶቻችን በሠሩት የትምህርት ሥርዓትም ምንኛ ጥበበኛ እንደ ሆኑ አስተውሉ! በቀን ጆሯችን የአካባቢ ድምጽ ይሰማል፤ ዓይናችን ሌላ ይመለከታል፤ ወጭ ወራጁ አላፊ አግዳሚው ይረብሻል። በሌሊት ግን ኅሊናን የሚሠርቅ ምንም ነገር የለምና ሐሳብን ሰብስቦ ለማስተማር እንዲመች የአብነት ትምህርቱን የሌሊትና የቀን ብለው ከፍለው የቃል ትምህርቱን በሌሊት እንድንማር አደረጉን። የጠቢቡ ሰሎሞን “ሌሊት በምንጣፌ ላይ ነፍሴ የወደደችውን ፈለግሁት” የሚለው ቃል ምነኛ ይደንቃል! (መኃ.፫፥፩) ኒቆዲሞስ ነፍሱ የፈለገችውን ሊፈልግ በሌሊት መጣ። ሌሊት ሁሉ ሰው ተኝቶ ባለበት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር መቻል እንዴት መታደል ነው። ክርስቲያኖች እስኪ አስቡት! ማንም በሌለበት፣ ሁሉ በተኛበት ሰዓት አልጋችሁ ላይ ሁናችሁ ክርስቶስን መፈለግ በጨለማ ውስጥ ውሳጣዊ ዓይናችሁ ብቻ ተከፍቶ ከአምላካችሁ ጋር መነጋገር እጅግ ልዩ ነውና ሌሊቱን ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን አሳልፉት።
ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ በመሆኑ ቀን ሥራ ውሎ ሌሊት በእግዚአብሔር ቃል ያርፍ ነበር። ይህ ሐሳብ ለእኛ ዘመንም የሚጠቅም ነውና እንማርበት ዘንድ ወደድኩኝ። ዛሬ የሕዝብ አለቃዎች ሹማምንቶች መኳንንቶች እናንተስ መቼ ነው የምትማሩ? የምትበልጠዋን ጸጋ ታገኟት ዘንድ ያገኛችኋትን ታጸኗት ዘንድ ኑ! የእግዚአብሔር አካል በሆነችዋ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል እየሰማችሁ ዕረፉ። ዛሬ ብዙ ሰው ለምን አትማርም ሲባል ሥራ በዝቶብኝ፣ ቢዚ ሁኜ በማለት መመለሱ እየተለመደ መጥቶአል። እኔ ግን እንዲህ ብዬ እጠይቃችኋለሁ፣ በውኑ የእናንተ ሥራ ከኒቆዲሞስ ይበልጣልን? ወይስ ከዳዊት በላይ ትሠራላችሁ? ወይንስ ከላል ይበላ በላይ ሠርታችሁ ነው? እኔ ግን በመኃልየ መኃልይ እንደ ተጻፈ በምክንያት እየራቃችሁ ነው። “እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፤ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ። ቀሚሴን አወለቅሁ፤ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፤ እንዴት አሳድፈዋለሁ?” በማለት እንደተናገረችው ሰው የሆን ይመስለኛል። (መኃ.፭፥፪) ይህች ሰው ከረፈደ በኋላ ፍለጋ ብትወጣም ማግኘት ግን አልቻለችም፤ እናም ሁላችንም ዛሬ ሳይረፍድብን ታግለን መጣል ሩጠን መቅደም በምንችልበት ጊዜ ምክንያት በመደርደር አንራቅ ለማለት እወዳለሁ።
ኒቆዲሞስ በሌሊት መጥቶ ከጌታችን እግር ሥር ተቀምጦ ሲማር በዓይነ ኅሊናችን እንመልከተው! ግርማ ሌሊቱ ጸብአ አራዊቱ ሳያስፈራው፣ ድካም ሳይበግረው በጌታው እግር ሥር ቁጭ ብሎ ሲማር ቅዱስ ዳዊት ” ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ። ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ። ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።” እንዳለ ከማርና ከሥኳር የሚጣፍጠውን ቃለ እግዚአብሔር ሲሰማ ሰው እንዳያየው ተደብቆ የመጣው ኒቆዲሞስ ከመስቀሉ ሥር የሚገኝ የመከራ ቀን ሐዋርያ ሆነ። (መዝ.፻፲፱፥፻፫-፻፭) ሌሊት በመከራ ይመሰላል፤ በመከራ መጥቶ የተማረው ኒቆዲሞስ ሐዋርያት እንኳን ጥለውት በሸሹ ጊዜ ከመስቀሉ ሥር ተገኘ። ሥጦታ ይሆን ዘንድ የክርስቶስን ሥጋ ገንዞ ለመቅበር የበቃ ሆነ። ክርስቲያኖች! እናንተስ ክርስቶስን ልትገንዙ ትሻላችሁን? በዚያ በመስቀል ላይ ሳለ ቅድስት ሥጋው ከቅድስት ነፍሱ ሲለይ ከመስቀል አውርዶ የሚቀብረው አጥቶ እናቱ ድንግል ማርያም እያለቀሰች ሳለ የተገኘ የእመ ብርሃንን እንባ ያበሰ ቅዱስ ለመሆን በቃ።
አሁንም እንደ ኒቆዲሞስ ሌሊት መጥቶ የሚማር ሰው አጥታ ቤተ ክርስቲያን ስታለቅስ፣ ሰቃልያነ ክርስቶስ ጌታን ዳግመኛ ሊሰቅሉት ሲሹ ከመስቀሉ ሥር የሚገኝ በመከራ የሚጸና ሰው ያስፈልጋልና የዓለም ውጣ ውረድ ሳያግዳችሁ ከቤቱ መጥታችሁ ትማሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ዛሬ ላይ አንድ ነገር ይደንቀኛል! ሰው ሥልጣን ሲይዝ ከቤተ ክርስቲያን የሚያደርገውን ሽሽት አስተውሉ! ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ቢሆንም ግን ወደ ጌታ ከመምጣት አላገደውም፤ የዛሬዎቹ አለቃ ግን አለመምጣት ብቻ ሳይሆን ክርስቲያን ሆኖ መታየት እንኳን ያሳፍራቸዋል። የልቤ እምነት እንጅ ማተብ ባላደርግስ በሚል ሐሳብም ማተባቸውን የሚፈቱም አይጠፉ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለመመሳሰል ሐብል ያደርጋሉ። ክርስቲያኖች ከአምላካችን በእውነት ወዴት እንሄዳለን? እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት “ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃል አለህ፤ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት” እንዲል፤ እንዲህ እያልን ልንኖር ያስፈልጋል፡፡ (ዮሐ ፮፥፷፰)
ሊቃውንቱም በቅኔያቸው ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አጽባእት እምነ አጽባእት የዓቢ፤ ….. በማለት ጣት ከእጣት እንዲበልጥ የአይሁድ ምሁር የነበረው ኒቆዲሞስ ለጌታችን እንደሰገደ ከቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ በመነሳት ይቀኛሉ። በመጨረሻም ኒቆዲሞስን መምህራችን አድርገን ቀን በሥራችን ስንባክን የምንውል እኛ ማታ ላይ የእግዚአብሔርን ቃል እንማር ምን አልባት እንደ አካብና ኤልዛቤል የሚያሳድደን ንጉሥ መጥቶ ራብተኞች እንዳንሆን፣ ዛሬ እንቅልፋችንን ቀንሰን ከኃጢአታችንን ነቅተን ቃለ እግዚአብሔር እንብላ ” የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ አለው” (፩ኛነገ.፲፱፥፯) እንዲል፡፡
አምላካችን በቸርነቱ ከእንቅልፋችንና ከኃጢአታችን ነቅተን ቃሉን እንደ ውኃ ተጥተን፣ እንደ ምግብ ተመግበን፣ እንድ መጎናፀፊያ ተጎናጽፈን እንድንኖር ይርዳን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክበር አሜን!!!
ምንጭ ፦ ማህበረ ቅዱሳን ድህረገጽ