በመክፈት ላይ

እንኳን ወደ ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ በሰላም መጡ !

እንኳን ወደ ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ በሰላም መጡ !

የሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ይመልከቱ

ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዩኬና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በማኅበርነት ሰባት ዓመታትን ቆይቷል። በእነዚህ ሰባት ዓመታት ውስጥ ምእመናን የራሳቸው አገልግጋይ እና አጽናኝ ካህን ወይም መምህር ሳይኖሯቸው ከሌሎች ከተሞች በሚመጡ ካህናትና መምህራን በመጽናናት እግዚአብሔርን ዘወትር በማገልገል ቆይተዋል።

እርስዎም ይምጡ ይሳተፉ

የተለያዩ መርሐ ግብራት ሲኖሩ መጥተው ይሳተፉ ዘንድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች!

አድራሻ

አኃዛዊ መረጃዎች

የምእመናን (የአባላት) ቁጥር
120
የአገልጋይ ቁጥር
8
የሰንበት ተማሪዎች ቁጥር
15
በዓመቱ የተጠመቁ ምእመናን
6

የቤተ ክርስቲያናችን አባል ይሁኑ

በሊቨርፑል እና አካባቢዋ የሚኖሩ ከሆነ የቤተ ክርስቲያናችን ቋሚ አባል በመሆን በየጊዜው በሚካሄዱ መርሐ ግብሮች ላይ እንዲሳተፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች::

ይመዝገቡ

የአብያተ ክርስቲያናት መረጃ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታላቋ ብሪታንያና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን መረጃ እዚህ ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

አብያተ ክርስቲያናትን ይመልከቱ

ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ፈላጊዎች

የበረከት ተካፋይ እና የታሪክ አካል ይሁኑ!

ቤተ ክርስቲያናችን የራሷ የሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት እየተጋች ነው።

የተለያዩ ምዕመናን በዚህ ታላቅ የታሪክ አሻራ ላይ አስተዋጽኦ እያደረጉ ሲሆን የቻሉ በቀጥታ ክፍያ፣ ያልቻሉ ደግሞ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል መጠን ለመክፈል ቃል እየገቡ ቀስ በቀስ በሂደት በመክፈል ላይ ይገኛሉ።

አሁን ላይ ያለንበት ሁኔታ

£186,037

ከ£450,000 ውስጥ

41.3%

የተከፈለ:
£104,682
ቃል የተገባ (ገና ያልተከፈለ):
£81,355

የቤተክርስቲያኑ ላይኛው ወለል

ቤተ ክርስቲያኑ 2 ወለል ያለው ሲሆን እያንዳንዱ ወለል 513m² ስፋት አለው። ምስሉ ላይ የምትመለከቱት እያንዳንዱ 1m × 1m ካሬ ዋጋው £400 ሲሆን፣ እስካሁን የተከፈለ ሲደመር ለመክፈል ቃል የተገባ ግን ያልተከፈለ የገንዘብ መጠን ይህ የተገለጸውን የወለሉን ክፍል መሸፈን አስችሏል።

ከ513 m² ውስጥ 465 m² ተሸፍኗል

ወቅታዊ ዜናዎች

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

በደብራችን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ።

በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት ኅዳር 21/2018 ዓ/ም በለንደን ጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀብለዋል።

1 ደቂቃ ንባብ

በአውሮፓ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ “የተክልዬ ተጓዦች” በሚል ስያሜ በኢንግላንድ ከስቶክ ኦን ትሬንት ወደ ሊቨርፑል በሚጓዙ ምእመናን ተጀመረ !

ቀደምት አባቶችን በመዘከር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዋወቅና የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ሐዋርያዊ ጉዞ ምክንያት በማድረግ ታላቋ ብሪታንያ በስቶክ ኦን ትሬንት ከተማ የሚገኙ የቅዱስ ሩፋኤል ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ መንፈሳዊ ማኅበር አባላት የፊታችን ቅዳሜ በሊቨርፑል ከአቡነ ተክለሃይማኖት የሚከበረውን የጻድቁን የዕረፍት በዓል ምክንያት በማድረግ በአውሮፓ አህጉር የመጀመሪያውን 18 ሰዓታት የሚወስደውን የእግር ጉዞ በዛሬው ዕለት ጀምረዋል። የእግር ጉዞው ነገ ዓርብ ከቀትር በኃላ ሊቨርፑል በመግባት እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ምእመናኑ በሚያልፉባቸው ከተሞች የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ሐዋርያዊ ጉዞ በማሰብ በየከተማው ለሚገኙ የሀገሪቱ ነዋሪዎች የጻድቁን ሕይወትና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማስተዋወቅ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ጉዞ የሚያደርጉ መሆኑ ነው የተገለጸው። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ምእመናን በዓይነቱ ልዩ የሆነውን እና ለበጎ ዓላማ የሚካሄደውን ይህንን መንፈሳዊ የእግር ጉዞ በማበረታታት ላይ እንደሚገኙ ነው የተጠቆመው። ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ለንደን)

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

ዜና ቤተክርስቲያን

በዛሬው ዕለት በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንየመጭውን የጻድቁ አባታችንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት ለሚደረገው ዝግጅት በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ጥረት የህንጻ ግዢ የገቢ አሰባሳቢክፍሉ በደብሩ ያሉትን የአገልግሎት ክፍሎች በጋራ ሊያሳካ ስለሚችለው ውይይት አድርጏል ለዚሁም ይረዳው ዘንድ በዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቅም ስልጠና ተሰጥቷል::