ቀጣይ መርሃግብር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን : በዐቢይ ኃይል ወስልጣን
አሠሮ ለሰይጣን : አግዐዞ ለአዳም
ሰላም : እምይእዜሰ
ኮነ : ፍስሃ ወሰላም
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ መንፈስ ቅዱስ) በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን::
የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአደራ ልጆች የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወዳጆች
ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በቀን 03/06/2023 ቅዳሜ በጧቱ 6:30 am በሊቨርፑል መካነ ቅዱሣን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የቅዳሴ መርሃ ግብራችን ስለሆነ፣ ሁላችንም በሰዓቱ ተገኝተን የቅዳሴው በረከት ተካፋዮች እንድንሆን ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
ለሌሎችም እንዲደርስ አጋሩ።
ለሀገራችን ብሎም ለቤተክርስቲያናችን ፍፁም ሰላምን ፍቅር አንድነትን ይስጥልን ይጠብቅልን።