በመክፈት ላይ

ማክሰኞ – ዕለተ ተስእሎ

ማክሰኞ – ዕለተ ተስእሎ

የሰሙነ ህማማት መንፈሳዊ ምግባራት መከታተያ ድህረ-ገጽን በመጠቀም በየቀኑ የሚደረጉ ተግባራትን ለማከናወን ይሞክሩ

የሰሙነ ሕማማት ኹለተኛ ቀን ማክሰኞ(ማግሰኞ) ጌታ በመቅደሱ ያደረገውን የማጽዳት ሥራ ተከትሎ ከአይሁድ አለቆች የቀረበለት ጥያቄና እርሱ በጥበብ የመለሰበት መንገድ የሚታሰብበት ነው።

ይህ ክፍል ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21፥23-27 ላይ የሚገኝ ሲሆን በሌሎቹ ወንጌላት ላይ ማር.11፥27/ሉቃ.20፥1-8 ላይ እናገኘዋለን።
ክርስቶስ ይህን መቅደሱን ከማይገባ የንግድ ሥራ ሲያጸዳ ኹለተኛ ጊዜው ሲሆን ጥያቄው የቀረበለት በዚህ ጊዜ ነበር።

“ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና፦ በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።” 21፥23

ይህ ጥያቄ ከአይሁድ አለቆች በተንኮል የቀረበ ጥያቄ ነው ስልጣኑ ከእግዚአብሔር ተሰጠኝ ቢል እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እንደማስተካከል አድርገው ስለሚቆጥሩት አምላክን ሰደበ ብለው ሞት ለመፍረድ ያመቸናል ብለው አስበው ነበር ከሰው ቢላቸው በሚከተሉት ሰዎች ፊት አናንቀው ተከታይና ሰሚ ለማሳጣት አስበው ነበረ ቢሆንም ክርስቶስ ግን በጥበብ በጥያቄ መለሰላቸው።

“የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው? አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ብንል፦ እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤” 21፥25

ክርስቶስ በአይሁድ ባህል ጥያቄን በጥያቄ መንገድ የመመለስን ዘይቤን ተጠቅሞ አጣብቂኝ ውስጥ ከተታቸው ከሰማይ እንዳይሉ በዮሐንስ ጥምቀት አያምኑበትም። ከዛም አልፎ የዮሐንስን ከሰማይ ካሉ መንገድ ጠራጊው የሆነለት ዮሐንስ የሰበከለት መሲሕ ክርስቶስ ከሰማይ ነው ብለው ለመቀበል ይገደዱ ነበር። ከሰው ነው ደግሞ እንዳይሉ ከሕዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊገጥማቸው ሆነ አብዛኛው ሕዝብ የዮሐንስን ጥምቀት ይቀበል ነበርና።

የክርስቶስ ስልጣን ከሰማይ እንጂ ከዚህ ምድር አልነበረም ስለ እርሱ ስለሚያደርግበት የስልጣም ምንጭ እየተጠየቀ ዮሐንስ ያጠምቅበት ስለነበረው ስልጣን መጠየቁ ይደንቃል እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል ያለለት ዮሐንስ፣ የጫማውን ጠፍር እፈታ ዘንድ የማይገባኝ ያለለት ዮሐንስ፣ እኔ በውኃ እርሱ ግን በእሳት ያጠምቃል ያለለት ፍርድ ገንዘቡ ለመሆኑ መንሹ በእጅ ነው ያለለት ዮሐንስ የማጥመቅ ስልጣኑ የተሰጠው ከእርሱ ሆኖ እንዴት የሰጩ ስልጣን ከምድር ሊሆን ይችላል?

እርሱንስ ቢያውቁት የመቅደሱ ጌታ ነው፣ ከነገድ ለይቶ ለመሥዋዕት ሥርዐቱ አሮንና ልጆቹን የጠራ እርሱ ነው፣ በመቅደሱ በጥላነት የሚሰውቱን ሁሉ ሊፈጽም የተገለጠ እርሱ ነው፣ ከመቅደስ የሚበልጠው መቅደስ እርሱ ነው። የመቅደሱ ሰዎች የመቅደሱን ጌታ ጠየቁት።

ዲያቆን ቡሩክ ተስፋዬ

ለሌሎች ያጋሩ

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

በደብራችን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ።

በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት ኅዳር 21/2018 ዓ/ም በለንደን ጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀብለዋል።

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

ዜና ቤተክርስቲያን

በዛሬው ዕለት በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንየመጭውን የጻድቁ አባታችንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት ለሚደረገው ዝግጅት በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ጥረት የህንጻ ግዢ የገቢ አሰባሳቢክፍሉ በደብሩ ያሉትን የአገልግሎት ክፍሎች በጋራ ሊያሳካ ስለሚችለው ውይይት አድርጏል ለዚሁም ይረዳው ዘንድ በዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቅም ስልጠና ተሰጥቷል::

ወቅታዊ

1 ደቂቃ ንባብ

ዜና ቤተክርስቲያን

በትናንትናው ዕለት ማለትም በ17/12/2017 ዓም (August 23/2025) በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አንድ አዲስ ነገር ተፈፅሟል ይኸውም ጀማል የተባለ ከእስልምና ወደ ክርስትና በመምጣት መስረታዊ የክርስትና ትምህርቱን በተገቢ መንገድ አጠናቅቆ የሥላሴ ልጅነቱን አግኝቷል ትምህርቱንም የሰጠው ዲያቆን ዘማርያም ሲሆን በደብራችንም ተጨማሪ ክትትል በማድረግ እነሆ ተከናውኗል እግዚአብሔር ይመስገን::