Current News
የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የፍልሠተ ዐፅሙ መታሰቢያ በዓል
ቅዳሜ ግንቦት 9/2017 ዓ.ም ወይም May 17/2025 የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የፍልሠተ አፅሙ መታሰቢያ በዓል ከጠዋቱ 5AM ጀምሮ በድምቀት ይከበራል።
Loading
Please choose your language
Church news, upcoming programmes and spiritual teaching, all in one place.
Current News
ቅዳሜ ግንቦት 9/2017 ዓ.ም ወይም May 17/2025 የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የፍልሠተ አፅሙ መታሰቢያ በዓል ከጠዋቱ 5AM ጀምሮ በድምቀት ይከበራል።
Current News
የሰሙነ ህማማት መንፈሳዊ ምግባራት መከታተያ ድህረ-ገጽን በመጠቀም በየቀኑ የሚደረጉ ተግባራትን ለማከናወን ይሞክሩ የሰሙነ ሕማማት ኹለተኛ ቀን ማክሰኞ(ማግሰኞ) ጌታ በመቅደሱ ያደረገውን የማጽዳት ሥራ ተከትሎ ከአይሁድ አለቆች የቀረበለት ጥያቄና እርሱ በጥበብ የመለሰበት መንገድ የሚታሰብበት ነው። ይህ ክፍል ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21፥23-27 ላይ የሚገኝ ሲሆን በሌሎቹ ወንጌላት ላይ ማር.11፥27/ሉቃ.20፥1-8 ላይ እናገኘዋለን።ክርስቶስ ይህን መቅደሱን ከማይገባ የንግድ ሥራ ሲያጸዳ ኹለተኛ ጊዜው ሲሆን ጥያቄው የቀረበለት በዚህ ጊዜ ነበር። “ወደ መቅደስም ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሎች ወደ እርሱ ቀረቡና፦ በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።” 21፥23 ይህ ጥያቄ ከአይሁድ አለቆች በተንኮል የቀረበ ጥያቄ ነው ስልጣኑ ከእግዚአብሔር ተሰጠኝ ቢል እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እንደማስተካከል አድርገው ስለሚቆጥሩት አምላክን ሰደበ ብለው ሞት ለመፍረድ ያመቸናል ብለው አስበው ነበር ከሰው ቢላቸው በሚከተሉት ሰዎች ፊት አናንቀው ተከታይና ሰሚ ለማሳጣት አስበው ነበረ ቢሆንም ክርስቶስ ግን በጥበብ በጥያቄ መለሰላቸው። “የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይን ወይስ ከሰው? አላቸው። እነርሱም እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፦ ከሰማይ ብንል፦ እንኪያስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤” 21፥25 ክርስቶስ በአይሁድ ባህል ጥያቄን በጥያቄ መንገድ የመመለስን ዘይቤን ተጠቅሞ አጣብቂኝ ውስጥ ከተታቸው ከሰማይ እንዳይሉ በዮሐንስ ጥምቀት አያምኑበትም። ከዛም አልፎ የዮሐንስን ከሰማይ ካሉ መንገድ ጠራጊው የሆነለት ዮሐንስ የሰበከለት መሲሕ ክርስቶስ ከሰማይ ነው ብለው ለመቀበል ይገደዱ ነበር። ከሰው ነው ደግሞ እንዳይሉ ከሕዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊገጥማቸው ሆነ አብዛኛው ሕዝብ የዮሐንስን ጥምቀት ይቀበል ነበርና። የክርስቶስ ስልጣን ከሰማይ እንጂ ከዚህ ምድር አልነበረም ስለ እርሱ ስለሚያደርግበት የስልጣም ምንጭ እየተጠየቀ ዮሐንስ ያጠምቅበት ስለነበረው ስልጣን መጠየቁ ይደንቃል እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል ያለለት ዮሐንስ፣ የጫማውን ጠፍር እፈታ ዘንድ የማይገባኝ ያለለት ዮሐንስ፣ እኔ በውኃ እርሱ ግን በእሳት ያጠምቃል ያለለት ፍርድ ገንዘቡ ለመሆኑ መንሹ በእጅ ነው ያለለት ዮሐንስ የማጥመቅ ስልጣኑ የተሰጠው ከእርሱ ሆኖ እንዴት የሰጩ ስልጣን ከምድር ሊሆን ይችላል? እርሱንስ ቢያውቁት የመቅደሱ ጌታ ነው፣ ከነገድ ለይቶ ለመሥዋዕት ሥርዐቱ አሮንና ልጆቹን የጠራ እርሱ ነው፣ በመቅደሱ በጥላነት የሚሰውቱን ሁሉ ሊፈጽም የተገለጠ እርሱ ነው፣ ከመቅደስ የሚበልጠው መቅደስ እርሱ ነው። የመቅደሱ ሰዎች የመቅደሱን ጌታ ጠየቁት። ዲያቆን ቡሩክ ተስፋዬ
Upcoming Programmes
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን ክርስቶስ ተንስአ እሙታን : በዐቢይ ኃይል ወስልጣንአሠሮ ለሰይጣን : አግዐዞ ለአዳምሰላም : እምይእዜሰኮነ : ፍስሃ ወሰላም እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ (በዓለ መንፈስ ቅዱስ) በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን:: የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአደራ ልጆች የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወዳጆች ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። በቀን 03/06/2023 ቅዳሜ በጧቱ 6:30 am በሊቨርፑል መካነ ቅዱሣን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የቅዳሴ መርሃ ግብራችን ስለሆነ፣ ሁላችንም በሰዓቱ ተገኝተን የቅዳሴው በረከት ተካፋዮች እንድንሆን ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ለሌሎችም እንዲደርስ አጋሩ። ለሀገራችን ብሎም ለቤተክርስቲያናችን ፍፁም ሰላምን ፍቅር አንድነትን ይስጥልን ይጠብቅልን።
Welcome to our website!
What may we help you with today?
Please wait a moment. We are connecting you with someone who can help you. Thank you for your patience.
This chat has ended. God bless you.