Loading

የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት – ሆሣዕና/ Hosanna

የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት – ሆሣዕና/ Hosanna

This post is only available in Amharic.

በዕለቱ የሚነበቡት መልዕክታት

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች:- ም. 9 ቊ. 11-ፍ.ም / St Paul’s letter to the Hebrews:- ch. 9 nu. 11-end

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች:- ም. 9 ቊ. 11-ፍ.ም

11፤ ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥

12፤ የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።

13፤ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥

14፤ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?

15፤ ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።

16፤ ኑዛዜ ያለ እንደሆነ የተናዛዡን ሞት ማርዳት የግድ ነውና፤

17፤ ሰው ሲሞት ኑዛዜው ይጸናልና፥ ተናዛዡ በሕይወት ሲኖር ግን ከቶ አይጠቅምም።

18፤ ስለዚህም ፊተኛው ኪዳን እንኳ ያለ ደም አልተመረቀም።

19-20፤ ሙሴም ትእዛዛትን ሁሉ እንደ ሕጉ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ፥ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውኃና ከቀይ የበግ ጠጕር ከሂሶጵም ጋር ይዞ፦ “እግዚአብሔር ያዘዘላችሁ የኪዳን ደም ይህ ነው፡” ብሎ በመጽሐፉና በሕዝቡ ሁሉ ላይ ረጨው።

21፤ እንዲሁም በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጨ።

22፤ እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።

23፤ እንግዲህ በሰማያት ያሉትን የሚመስለው ነገር በዚህ ሊነጻ እንጂ በሰማያት ያሉቱ ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መሥዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ።

24፤ ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።

25፤ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤

26፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።

27፤ ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥

28፤ እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።

St Paul’s letter to the Hebrews:- ch. 9 nu. 11-end

11. But Christ being come an high priest of good things to come, by a greater and more perfect tabernacle, not made with hands, that is to say, not of this building;

12. Neither by the blood of goats and calves, but by his own blood he entered in once into the holy place, having obtained eternal redemption for us.

13. For if the blood of bulls and of goats, and the ashes of an heifer sprinkling the unclean, sanctifieth to the purifying of the flesh:

14. How much more shall the blood of Christ, who through the eternal Spirit offered himself without spot to God, purge your conscience from dead works to serve the living God?

15. And for this cause he is the mediator of the new testament, that by means of death, for the redemption of the transgressions that were under the first testament, they which are called might receive the promise of eternal inheritance.

16. For where a testament is, there must also of necessity be the death of the testator.

17. For a testament is of force after men are dead: otherwise it is of no strength at all while the testator liveth.

18. Whereupon neither the first testament was dedicated without blood.

19. For when Moses had spoken every precept to all the people according to the law, he took the blood of calves and of goats, with water, and scarlet wool, and hyssop, and sprinkled both the book, and all the people,

20. Saying, This is the blood of the testament which God hath enjoined unto you.

21. Moreover he sprinkled with blood both the tabernacle, and all the vessels of the ministry.

22. And almost all things are by the law purged with blood; and without shedding of blood is no remission.

23. It was therefore necessary that the patterns of things in the heavens should be purified with these; but the heavenly things themselves with better sacrifices than these.

24. For Christ is not entered into the holy places made with hands, which are the figures of the true; but into heaven itself, now to appear in the presence of God for us:

25. Nor yet that he should offer himself often, as the high priest entereth into the holy place every year with blood of others;

26. For then must he often have suffered since the foundation of the world: but now once in the end of the world hath he appeared to put away sin by the sacrifice of himself.

27. And as it is appointed unto men once to die, but after this the judgment:

28. So Christ was once offered to bear the sins of many; and unto them that look for him shall he appear the second time without sin unto salvation.

የጴጥሮስ መልዕክት:- ም. 4 ቊ. 1-12 / St Peter’s First letter:- ch. 4 nu. 1-12

የጴጥሮስ መልዕክት:- ም. 4 ቊ. 1-12

1-2፤ ክርስቶስም በሥጋ ስለ እኛ መከራን ስለተቀበለ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ፥ እናንተ ደግሞ ያን አሳብ እንደ ዕቃ ጦር አድርጋችሁ ያዙት፥ በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአልና።

3፤ የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።

4፤ በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤

5፤ ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።

6፤ እንደሰዎች በሥጋ እንዲፈረድባቸው በመንፈስ ግን እንደ እግዚአብሔር እንዲኖሩ ስለዚህ ምክንያት ወንጌል ለሙታን ደግሞ ተሰብኮላቸው ነበርና።

7፤ ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፥

8፤ ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።

9፤ ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤

10፤ ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤

11፤ ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።

12፤ ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤

St Peter’s First letter:- ch. 4 nu. 1-12

1. Forasmuch then as Christ hath suffered for us in the flesh, arm yourselves likewise with the same mind: for he that hath suffered in the flesh hath ceased from sin;

2. That he no longer should live the rest of his time in the flesh to the lusts of men, but to the will of God.

3. For the time past of our life may suffice us to have wrought the will of the Gentiles, when we walked in lasciviousness, lusts, excess of wine, revellings, banquetings, and abominable idolatries:

4. Wherein they think it strange that ye run not with them to the same excess of riot, speaking evil of you:

5. Who shall give account to him that is ready to judge the quick and the dead.

6. For for this cause was the gospel preached also to them that are dead, that they might be judged according to men in the flesh, but live according to God in the spirit.

7. But the end of all things is at hand: be ye therefore sober, and watch unto prayer.

8. And above all things have fervent charity among yourselves: for charity shall cover the multitude of sins.

9. Use hospitality one to another without grudging.

10. As every man hath received the gift, even so minister the same one to another, as good stewards of the manifold grace of God.

11. If any man speak, let him speak as the oracles of God; if any man minister, let him do it as of the ability which God giveth: that God in all things may be glorified through Jesus Christ, to whom be praise and dominion for ever and ever. Amen.

12. Beloved, think it not strange concerning the fiery trial which is to try you, as though some strange thing happened unto you:

የሐዋርያት ሥራ:- ም. 28 ቊ. 11-ፍ.ም / Acts of The Apostles:- ch. 28 nu. 11-end

የሐዋርያት ሥራ:- ም. 28 ቊ. 11-ፍ.ም

11፤ ከሦስት ወርም በኋላ በደሴቲቱ ከርሞ በነበረው በእስክንድርያው መርከብ ተነሣን፥ በእርሱም የዲዮስቆሮስ አላማ ነበረበት።

12፤ ወደ ሰራኩስም በገባን ጊዜ ሦስት ቀን ተቀመጥን፤

13፤ ከዚያም እየተዛወርን ወደ ሬጊዩም ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላም የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ በሁለተኛው ቀን ወደ ፑቲዮሉስ መጣን።

14፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተን በእነርሱ ዘንድ ሰባት ቀን እንድንቀመጥ ለመኑን፤ እንዲሁም ወደ ሮሜ መጣን።

15፤ ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ሰምተው እስከ አፍዩስ ፋሩስና ሦስት ማደሪያ እስከሚባለው ሊቀበሉን ወጡ፥ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ ልቡም ተጽናና።

16፤ ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ተፈቀደለት።

17፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ጳውሎስ የአይሁድን ታላላቆች ወደ እርሱ ጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ሕዝቡን ወይም የአባቶችን ሥርዓት የሚቃወም አንዳች ሳላደርግ፥ ከኢየሩሳሌም እንደ ታሰርሁ በሮማውያን እጅ አሳልፈው ሰጡኝ።

18፤ እነርሱም መርምረው ለሞት የሚገባ ምክንያት ስላልነበረብኝ ሊፈቱኝ አሰቡ፤

19፤ አይሁድ ግን በተቃወሙ ጊዜ፥ ወደ ቄሣር ይግባኝ እንድል ግድ ሆነብኝ እንጂ ሕዝቤን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም።

20፤ ስለዚህም ምክንያት አያችሁና እነግራችሁ ዘንድ ጠራኋችሁ፤ ስለ እስራኤል ተስፋ ይህን ሰንሰለት ለብሻለሁና።”

21፤ እነርሱም፦ “እኛ ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልተቀበልንም፥ ከወንድሞችም አንድ ስንኳ መጥቶ ስለ አንተ ክፉ ነገር አላወራልንም ወይም አልተናገረብህም።

22፤ ነገር ግን ስለዚህ ወገን በየስፍራው ሁሉ እንዲቃወሙ በእኛ ዘንድ ታውቆአልና የምታስበውን ከአንተ እንሰማ ዘንድ እንፈቅዳለን፡” አሉት።

23፤ ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር።

24፤ እኵሌቶቹም የተናገረውን አመኑ፥ እኵሌቶቹ ግን አላመኑም፤

25፤ እርስ በርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳይያስ ለአባቶቻችን፦

26፤ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና፦ “መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤

27፤ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል፡” በላቸው፡’

28፤ ሲል መልካም ተናገረ። እንግዲህ ይህ የእግዚአብሔር ደኅንነት ለአሕዛብ እንደ ተላከ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ እነርሱ ደግሞ ይሰሙታል።”

29፤ ይህንም በተናገረ ጊዜ አይሁድ እርስ በርሳቸው እጅግ እየተከራከሩ ሄዱ።

30፤ ጳውሎስም በተከራየው ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፥ ወደ እርሱም የሚመጡትን ሁሉ ይቀበል ነበር፤

31፤ ማንም ሳይከለክለው የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እጅግ ገልጦ ያስተምር ነበር።

Acts of The Apostles:- ch. 28 nu. 11-end

11. And after three months we departed in a ship of Alexandria, which had wintered in the isle, whose sign was Castor and Pollux.

12. And landing at Syracuse, we tarried there three days.

13. And from thence we fetched a compass, and came to Rhegium: and after one day the south wind blew, and we came the next day to Puteoli:

14. Where we found brethren, and were desired to tarry with them seven days: and so we went toward Rome.

15. And from thence, when the brethren heard of us, they came to meet us as far as Appii forum, and The three taverns: whom when Paul saw, he thanked God, and took courage.

16. And when we came to Rome, the centurion delivered the prisoners to the captain of the guard: but Paul was suffered to dwell by himself with a soldier that kept him.

17. And it came to pass, that after three days Paul called the chief of the Jews together: and when they were come together, he said unto them, Men and brethren, though I have committed nothing against the people, or customs of our fathers, yet was I delivered prisoner from Jerusalem into the hands of the Romans.

18. Who, when they had examined me, would have let me go, because there was no cause of death in me.

19. But when the Jews spake against it, I was constrained to appeal unto Caesar; not that I had ought to accuse my nation of.

20. For this cause therefore have I called for you, to see you, and to speak with you: because that for the hope of Israel I am bound with this chain.

21. And they said unto him, We neither received letters out of Judaea concerning thee, neither any of the brethren that came shewed or spake any harm of thee.

22. But we desire to hear of thee what thou thinkest: for as concerning this sect, we know that every where it is spoken against.

23. And when they had appointed him a day, there came many to him into his lodging; to whom he expounded and testified the kingdom of God, persuading them concerning Jesus, both out of the law of Moses, and out of the prophets, from morning till evening.

24. And some believed the things which were spoken, and some believed not.

25. And when they agreed not among themselves, they departed, after that Paul had spoken one word, Well spake the Holy Ghost by Esaias the prophet unto our fathers,

26. Saying, Go unto this people, and say, Hearing ye shall hear, and shall not understand; and seeing ye shall see, and not perceive:

27. For the heart of this people is waxed gross, and their ears are dull of hearing, and their eyes have they closed; lest they should see with their eyes, and hear with their ears, and understand with their heart, and should be converted, and I should heal them.

28. Be it known therefore unto you, that the salvation of God is sent unto the Gentiles, and that they will hear it.

29. And when he had said these words, the Jews departed, and had great reasoning among themselves.

30. And Paul dwelt two whole years in his own hired house, and received all that came in unto him,

31. Preaching the kingdom of God, and teaching those things which concern the Lord Jesus Christ, with all confidence, no man forbidding him.

ምስባክ

እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሉከ ስብሐተ፡
በእንተ ጸላኢ፤
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ።
መዝሙር:- ፰: ፪

ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥
ስለ ጠላትህ፥
ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።
መዝሙር:- 8:2

Out of the mouth of babes and sucklings hast thou ordained strength,
because of thine enemies,
that thou mightest still the enemy and the avenger.
Psalms:- 8:2

ወንጌል / Gospel

ዮሐንስ:- ም. ፲፪(12) ቊ. ፲፪(12)-፳(20) / John :- ch. 12 nu. 12-20

ዮሐንስ:- ም. ፲፪(12) ቊ. ፲፪(12)-፳(20) </br> John :- ch. 12 nu. 12-20

12፤ በማግሥቱ ወደ በዓሉ መጥተው የነበሩ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ በሰሙ ጊዜ፥

13፤ የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ “ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው፡” እያሉ ጮኹ።

14-15፤ “አንቺ የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አግኝቶ በእርሱ ተቀመጠ።

16፤ ደቀ መዛሙርቱም ይህን ነገር በመጀመሪያ አላስተዋሉም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከከበረ በኋላ በዚያን ጊዜ ይህ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይህንም እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው።

17፤ አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር።

18፤ ስለዚህ ደግሞ ሕዝቡ ይህን ምልክት እንዳደረገ ስለ ሰሙ ሊቀበሉት ወጡ።

19፤ ሰለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፦ “አንድ ስንኳ ልታደርጉ እንዳይቻላችሁ ታያላችሁን? እነሆ፥ ዓለሙ በኋላው ተከትሎት ሄዶአል፡” ተባባሉ።

20፤ በበዓሉም ሊሰግዱ ከወጡት አንዳንዶቹ የግሪክ ሰዎች ነበሩ፤

John :- ch. 12 nu. 12-20

12. On the next day much people that were come to the feast, when they heard that Jesus was coming to Jerusalem,

13. Took branches of palm trees, and went forth to meet him, and cried, Hosanna: Blessed is the King of Israel that cometh in the name of the Lord.

14. And Jesus, when he had found a young ass, sat thereon; as it is written,

15. Fear not, daughter of Sion: behold, thy King cometh, sitting on an ass’s colt.

16. These things understood not his disciples at the first: but when Jesus was glorified, then remembered they that these things were written of him, and that they had done these things unto him.

17. The people therefore that was with him when he called Lazarus out of his grave, and raised him from the dead, bare record.

18. For this cause the people also met him, for that they heard that he had done this miracle.

19. The Pharisees therefore said among themselves, Perceive ye how ye prevail nothing? behold, the world is gone after him.

20. And there were certain Greeks among them that came up to worship at the feast:

ቅዳሴ / Liturgy

ቅዳሴ:- ዘጎርጎርዮስ
Anaphora:- St Gregory

ፈጣሬ ዓለማት አምላካችን እግዚአብሔር ምድርን ከነልብሱ ሰማይን ከነግሳንግሱ ፈጥሮ ብቻ አልተወም፤ ገዣቸው ይሆን ዘንድ በመጨረሻው የፍጥረት ቀን አዳምን በእጁ አበጃጀው እንጂ። ፈጥሮም የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ አለበት። አዳምም ሕያው ፍጥረት ሆነ። እንዲነዳቸው፣ እንዲገዛቸው ልዑል እግዚአብሔር አዳምን በፍጥረታት ላይ በመሾም ኃጢአት በማይደርስባት ገነት በግርማ አስቀመጠው።

አዳም እግዚአብሔር ያዘዘውን ረሳ፤ በእርሱና በእግዚአብሔር መካከል ለመታዘዝ ምልክት እንድትሆን የተነገረውን ዕፀ በለስ ሊቆርጥ ተነሣ። በመጨረሻም እጁን ልኮ ቆረጠ፤ በላም፤ በመብላቱም ወደቀ፤ ከገነትም ተባረረ።

ከገነት ለተባረረው አዳም በደሉን ይቅር ይለው ዘንድ እግዚአብሔር ከሰው ተወለደ፤ የሰውን ሥጋና ነፍስ ተዋሐደ፤ ወደ ግብጽ ተሰደደ፤ በኋላም በዮርዳኖስ ተጠመቀ፤ ከተጠመቀም በኋላ ብሕትውናንና የገዳም ሕይወትን ሊያስተምር ወደ ገዳመ ቆረንጦስ ሄደ። ከ፵ ቀን በኋላም ተመልሶ ደቀ መዛሙርትን ማስተማር ጀመረ፤ ይህ ሂደት ሦስት ዓመት ዘለቀ፤ የጌታችን ዕድሜም ሠላሳ ሦስት ዓመት ሞላ።

ጌታችን ከተወለደ ፴፫ የምሕረት ዘመናት ተቆጠሩ። ዕለቱ እሑድ፣ ቀኑ መጋቢት ፳፪ ነበር። በምድር የሚመላለስበትን ዘመን ሊጨርስ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ለደብረ ዘይት ትራራ ቅርብ ወደ ሆነችው ቤተ ፋጌና ቢታንያ መንደር ገሰገሰ፡፡ ከደቀ መዛሙርቱም ጴጥሮስና ዮሐንስን እንዲህ አላቸው፤ ‘‘በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደርም በገባችሁ ጊዜ ሰው በላዩ ያልተቀመጠበት የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፍቱና አምጡልኝ፤ ምን ታደርጋላችሁ የሚላችሁ ሰው ቢኖርም ጌታው ይሻዋል በሉ’’ አላቸው፤ (ማር.፲፩፥፪) ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም እንደታዘዙት አደርጉ፡፡

የታሰሩትን ሊፈታ መጥቱዋልና የታሰርውን ፍቱልኝ አለ፤ ሰውን ሁሉ ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈታበት ጊዜ እንደደረሰ ሲያጠይቅ ነው። በአህያ ላይ ሁኖ ሲገባም የሚበዙት ሕዝብ ለጌታችን ክብር ለአህያዋ ልብሳቸውን ጎዘጎዙ፤ ልብስ ገላን ይሸፍናልና ከባቴ አበሳ ነህ ሲሉ። በፊት በኋላ ሁነው ‘‘ለወልደ ዳዊት መድኃኒት መባል ይገባዋል’’ እያሉ አመሰገኑ፤ ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነውና “ሆሣዕና በአርያም” ሲሉ ቀኑን ዋሉ፡፡ በፊቱ ያሉት የሐዋርያት በኋላው ያሉት የነቢያት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በሌላም ትርጉም የብሉያትና የሐዲሳት ምሳሌዎች ሁነዋል። በዚህም የፊተኛውም የኋኛውም ዘመን ጌታ መሆኑ ተገልጧል፡፡

ሕዝቡ ሲዘምሩ የያዙት የዘንባባ ዝንጣፊም ጥንቱን አባቶቹ በብሉይ በዘንባባ ይገለገሉበት የነበረውን ያሳያል፤ እነ አብርሃምና እነ ይስሐቅ ሲወለዱ የዘንባባ ሰሌን ይዘረጋላቸው ነበርና። እሥራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ ዮዲት ሆሎፎርኒስን በገደለች ጊዜ ሰሌን ይዘው አመስግነው ነበርና። እሾህ አለው ትእምርተ ኃይል ትእምርተ መዊዕ አለህ ማለታቸው ነው። (ትር. ወን. ዘማቴዎስ)

ወደ ቤተ መቅደሱ ሲደርስም ሁለት ክፋቶች ተስተውለዋል። ቤተ መቅደሱን ለንግድ መገበያያነት ያዋሉት እና ለጌታችን ምስጋና እንዳይቀርብ ሲከለክሉ የታዩ የቤተ መቅደሱ አካባቢ ሰዎች ነበሩ፡፡ ጌታችን ለሁለቱም መልስ ሰጠ። የምስጋና መቅደሱን ለመገበያያነት ያደረጉትን ‘‘ቤቴ የጸሎት ቤት ነው’’ ብሎ እርግብና ዋኖሳቸውን ገለባብጦ አባረራቸው፡፡ (ዮሐ.፪፥፲፮) ምስጋና የከለከሉትንም አስገድዶ ራሱን አያስመልክምና “እናንት ባታመሰግኑኝ የቢታንያ ድንጋዮች ያመሰኙኛል” ብሎ ምስጋናው በፍጥረት ሁሉ ዘንድ እንጂ ከሰው ወገን ብቻ አለመሆኑን ግዑዛኑን ድንጋዮች ለምስጋና አስነሥቷል፡፡ ካህናቱ ቢከለክሉም ሕፃናቱን አበረታቸው። በዚህም ማንም የእግዚአብሔርን ምስጋና ሊከለክል እንደማይችል በሚገባ አሳያቸው።

ቤተ ክርስቲያንን ለግል ጥቅም የሚያውሉ ሰዎች ከቤተ ፋጌ ነጋዴዎች መማር አለባቸው። ጌታም በዕለተ ሆሣዕና ያስተማረው ይህን ነው። በሐዋርያት እግር የተተኩ ጳጳሳትና ሊቃውንት ባያስቆሙ እንኳን በገነት መግቢያ ሚዛን  ተመዝነው መውደቃቸው እሙን ነው። ማንም የአገልግሎት ስፍራን ከጸሎት ይልቅ ለጥቅም፣ ከምስጋና ይልቅ ለክርክርና ጭቅጭቅ ቢያውል እንደ ቤተ ፋጌዋ ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ፈታሒ በርትዕ ኮናኒ በጽድቅ ነውና በጥበቡ ለይቶ ያባርራል። መች እንድሚቀጣ እርሱ ያውቃል።

እግዚአብሔር ለምስጋና የሚሰለፉትን እየመረጠ ምስጋናውን የሚያስተጓጉሉትን በሌሎች እየተካ ዓለም ታልፋለች። ለምስጋና ለሚሰለፉት መንግሥተ ሰማይ ትተካለች። ምስጋናውን ሲያደናቅፉ ለነበሩ እንደ ቤተ ፋጌ ነጋዴዎችና አናመሰግንም ብለው አፋቸውን እንደዘጉ ምቀኞች ከርስታቸው ሰማያዊቷ ቤት ወጥተው ከእግዚአብሔር ቤት ተለይተው ገሃነመ እሳት ይወርዳሉ። ጉልበት ሳይደክም ወደ ገዳማት ማጓዝ፣ ዐይን ሳይፈዝ ለጸሎት መትጋት፣ ጀሮ ሳይደነዝዝ ቃለ እግዚአብሔርን መስማት፣ ምላስ ሳይታሰር ለምስጋና መትጋት ይገባል። ይህ ከሆነ ወደ በእግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንጂ በሆሣዕና እንደሆነው ሁሉ ወደፊት ገነትን በሚጠብቁ ልዑላን መላእክት በእሳት ሰይፍ እየተባረሩ በሰይጣን ሠራዊት እየተንገላቱ ወደ ሲዖል መውረድ የለም። ምስጋናውን ሲከለክሉ ዕድላቸው እንደተወሰደባቸው ሳይሆን ለምስጋና የዘንባባ ዝንጣፊ እንድያዙት ያድርገን። ቤተ መቅደሱን ለንግድ ሳይሆን ያለንን ጨርቅ እንኳን ለጌታችን ክብር የምናነጥፍበት የተሰበረ ልብ  ያድለን፤ አሜን!

ምንጭ ፦ ማህበረ ቅዱሳን ድህረገጽ

Share this post

Current News

1 min read

በደብራችን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ።

በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት ኅዳር 21/2018 ዓ/ም በለንደን ጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀብለዋል።

Current News

1 min read

ዜና ቤተክርስቲያን

በዛሬው ዕለት በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንየመጭውን የጻድቁ አባታችንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት ለሚደረገው ዝግጅት በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ጥረት የህንጻ ግዢ የገቢ አሰባሳቢክፍሉ በደብሩ ያሉትን የአገልግሎት ክፍሎች በጋራ ሊያሳካ ስለሚችለው ውይይት አድርጏል ለዚሁም ይረዳው ዘንድ በዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቅም ስልጠና ተሰጥቷል::

Current News

1 min read

ዜና ቤተክርስቲያን

በትናንትናው ዕለት ማለትም በ17/12/2017 ዓም (August 23/2025) በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አንድ አዲስ ነገር ተፈፅሟል ይኸውም ጀማል የተባለ ከእስልምና ወደ ክርስትና በመምጣት መስረታዊ የክርስትና ትምህርቱን በተገቢ መንገድ አጠናቅቆ የሥላሴ ልጅነቱን አግኝቷል ትምህርቱንም የሰጠው ዲያቆን ዘማርያም ሲሆን በደብራችንም ተጨማሪ ክትትል በማድረግ እነሆ ተከናውኗል እግዚአብሔር ይመስገን::