የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት – ደብረ ዘይት / Mount Olives
This post is only available in Amharic.
በዕለቱ የሚነበቡት መልዕክታት
የጳውሎስ መልዕክት ወደ ተሰሎንቄ የመጀመሪያው:- ም. 4 ቊ. 13-ፍ.ም / St Paul’s First letter to Thessalonians:- ch. 4 nu. 13-end
የመጀመሪያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ተሰሎንቄ:- ም. 4 ቊ. 13-ፍ.ም
13፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።
14፤ ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።
15፤ በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤
16፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
17፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
18፤ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።
St Paul’s First letter to Thessalonians:- ch. 4 nu. 13-end
13. But I would not have you to be ignorant, brethren, concerning them which are asleep, that ye sorrow not, even as others which have no hope.
14. For if we believe that Jesus died and rose again, even so them also which sleep in Jesus will God bring with him.
15. For this we say unto you by the word of the Lord, that we which are alive and remain unto the coming of the Lord shall not prevent them which are asleep.
16. For the Lord himself shall descend from heaven with a shout, with the voice of the archangel, and with the trump of God: and the dead in Christ shall rise first:
17. Then we which are alive and remain shall be caught up together with them in the clouds, to meet the Lord in the air: and so shall we ever be with the Lord.
18. Wherefore comfort one another with these words.
ሁለተኛው የጴጥሮስ መልዕክት:- ም. 3 ቊ. 7-15 / St Peter’s Second letter:- ch. 3 nu. 7-15
ሁለተኛው የጴጥሮስ መልዕክት:- ም. 3 ቊ. 7-15
7፤ አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።
8፤ እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
9፤ ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
10፤ የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
11-12፤ ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤
13፤ ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።
14፤ ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥
15፤ የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ።
St Peter’s Second letter:- ch. 3 nu. 7-15
7. But the heavens and the earth, which are now, by the same word are kept in store, reserved unto fire against the day of judgment and perdition of ungodly men.
8. But, beloved, be not ignorant of this one thing, that one day is with the Lord as a thousand years, and a thousand years as one day.
9. The Lord is not slack concerning his promise, as some men count slackness; but is longsuffering to us-ward, not willing that any should perish, but that all should come to repentance.
10. But the day of the Lord will come as a thief in the night; in the which the heavens shall pass away with a great noise, and the elements shall melt with fervent heat, the earth also and the works that are therein shall be burned up.
11. Seeing then that all these things shall be dissolved, what manner of persons ought ye to be in all holy conversation and godliness,
12. Looking for and hasting unto the coming of the day of God, wherein the heavens being on fire shall be dissolved, and the elements shall melt with fervent heat?
13. Nevertheless we, according to his promise, look for new heavens and a new earth, wherein dwelleth righteousness.
14. Wherefore, beloved, seeing that ye look for such things, be diligent that ye may be found of him in peace, without spot, and blameless.
15. And account that the longsuffering of our Lord is salvation; even as our beloved brother Paul also according to the wisdom given unto him hath written unto you;
የሐዋርያት ሥራ:- ም. 24 ቊ. 1-22 / Acts of The Apostles:- ch. 24 nu. 1-22
የሐዋርያት ሥራ:- ም. 24 ቊ. 1-22
1፤ ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት።
2-3፤ በተጠራም ጊዜ ጠርጠሉስ ይከሰው ዘንድ ጀመረ እንዲህ እያለ፦ “ክቡር ፊልክስ ሆይ፥ በአንተ በኩል ብዙ ሰላም ስለምናገኝ ለዚህም ሕዝብ በአሳብህ በየነገሩ በየስፍራውም መልካም መሻሻል ስለሚሆንለት፥ በፍጹም ምስጋና እንቀበለዋለን።
4፤ ነገር ግን እጅግ እንዳላቆይህ በቸርነትህ በአጭሩ ትሰማን ዘንድ እለምንሃለሁ።
5፤ ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና፤
6፤ መቅደስንም ደግሞ ሊያረክስ ሲሞክር ያዝነው፥ እንደ ሕጋችንም እንፈርድበት ዘንድ ወደድን።
7፤ ነገር ግን የሻለቃው ሉስዮስ መጥቶ በብዙ ኃይል ከእጃችን ወሰደው፥
8፤ ከሳሾቹንም ወደ አንተ ይመጡ ዘንድ አዘዘ፤ አንተም ራስህ እርሱን መርምረህ እኛ ስለምንከስበት ነገር ሁሉ ልታውቅ ትችላለህ።”
9፤ አይሁድም ደግሞ፦ “ይህ ነገር እንዲሁ ነው፡” እያሉ ተስማሙ።
10፤ ገዡም በጠቀሰው ጊዜ ጳውሎስ መለሰ እንዲህ ሲል፦ “ከብዙ ዘመን ጀምረህ ለዚህ ሕዝብ አንተ ፈራጅ እንደ ሆንህ አውቃለሁና ደስ እያለኝ ስለ እኔ ነገር እመልሳለሁ፤
11፤ እሰግድ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከአሥራ ሁለት ቀን እንዳይበልጥ ልታውቀው ትችላለህ።
12፤ ከአንድም ስንኳ ስነጋገር ወይም ሕዝብን ስሰበስብ በመቅደስ ቢሆን በምኵራብም ቢሆን በከተማም ቢሆን አላገኙኝም።
13፤ አሁንም ስለሚከሱኝ ያስረዱህ ዘንድ አይችሉም።
14፤ ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
15፤ እነዚህም ራሳቸው ደግሞ የሚጠብቁት፥ ጻድቃንም ዓመፀኞችም ከሙታን ይነሡ ዘንድ እንዳላቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ዘንድ አለኝ።
16፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።
17፤ ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤
18፤ ይህንም ሳደርግ ሳለሁ ሕዝብ ሳይሰበሰብ ሁከትም ሳይሆን በመቅደስ ስነጻ አገኙኝ።
19፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ነገር ያላቸው እንደ ሆነ፥ በፊትህ መጥተው ይከሱኝ ዘንድ የሚገባቸው ከእስያ የመጡ አንዳንድ አይሁድ አሉ።
20-21፤ ወይም በመካከላቸው ቆሜ፦ ‘ዛሬ ስለ ሙታን መነሣት በፊታችሁ በእኔ ይፈርዱብኛል’ ብዬ ከጮኽሁት ከዚህ ከአንድ ነገር በቀር፥ በሸንጎ ፊት ቆሜ ሳለሁ በእኔ አንድ ዓመፃ ያገኙ እንደ ሆን እነዚህ ራሳቸው ይናገሩ።”
22፤ ፊልክስ ግን የመንገዱን ነገር አጥብቆ አውቆአልና፦ “የሻለቃው ሉስዮስ በወረደ ጊዜ ነገራችሁን እቆርጣለሁ፡” ብሎ ወደ ፊት አዘገያቸው።
Acts of The Apostles:- ch. 24 nu. 1-22
1. And after five days Ananias the high priest descended with the elders, and with a certain orator named Tertullus, who informed the governor against Paul.
2. And when he was called forth, Tertullus began to accuse him, saying, Seeing that by thee we enjoy great quietness, and that very worthy deeds are done unto this nation by thy providence,
3. We accept it always, and in all places, most noble Felix, with all thankfulness.
4. Notwithstanding, that I be not further tedious unto thee, I pray thee that thou wouldest hear us of thy clemency a few words.
5. For we have found this man a pestilent fellow, and a mover of sedition among all the Jews throughout the world, and a ringleader of the sect of the Nazarenes:
6. Who also hath gone about to profane the temple: whom we took, and would have judged according to our law.
7. But the chief captain Lysias came upon us, and with great violence took him away out of our hands,
8. Commanding his accusers to come unto thee: by examining of whom thyself mayest take knowledge of all these things, whereof we accuse him.
9. And the Jews also assented, saying that these things were so.
10. Then Paul, after that the governor had beckoned unto him to speak, answered, Forasmuch as I know that thou hast been of many years a judge unto this nation, I do the more cheerfully answer for myself:
11. Because that thou mayest understand, that there are yet but twelve days since I went up to Jerusalem for to worship.
12. And they neither found me in the temple disputing with any man, neither raising up the people, neither in the synagogues, nor in the city:
13. Neither can they prove the things whereof they now accuse me.
14. But this I confess unto thee, that after the way which they call heresy, so worship I the God of my fathers, believing all things which are written in the law and in the prophets:
15. And have hope toward God, which they themselves also allow, that there shall be a resurrection of the dead, both of the just and unjust.
16. And herein do I exercise myself, to have always a conscience void of offence toward God, and toward men.
17. Now after many years I came to bring alms to my nation, and offerings.
18. Whereupon certain Jews from Asia found me purified in the temple, neither with multitude, nor with tumult.
19. Who ought to have been here before thee, and object, if they had ought against me.
20. Or else let these same here say, if they have found any evil doing in me, while I stood before the council,
21. Except it be for this one voice, that I cried standing among them, Touching the resurrection of the dead I am called in question by you this day.
22. And when Felix heard these things, having more perfect knowledge of that way, he deferred them, and said, When Lysias the chief captain shall come down, I will know the uttermost of your matter.
ምስባክ
እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ።
ወአምላክነሂ ኢያረምም፡
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ።
መዝሙር:- ፵፱: ፪-፫
እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል።
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤
እሳት በፊት ይቃጠላል።
መዝሙር:- 50:2-3
Our God shall come,
and shall not keep silence:
a fire shall devour before him.
Psalms:- 50:3
ወንጌል / Gospel
ማቴዎስ:- ም. ፳፬(24) ቊ. ፩(1)-፴፮(36) / Mathew:- ch. 24 nu. 1-36
ማቴዎስ:- ም. ፳፬(24) ቊ. ፩(1)-፴፮(36)
1፤ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
2፤ እርሱ ግን መልሶ፦ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡” አላቸው።
3፤ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ “ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?” አሉት።
4፤ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
5፤ ብዙዎች፦ ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ’ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
6፤ “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
7፤ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
8፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
9፤ “በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
10፤ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤
11፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
12፤ “ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።
13፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
14፤ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።”
15፤ “እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥
16፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥
17፤ በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥
18፤ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።
19፤ በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።
20፤ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤
21፤ “በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።
22፤ እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።
23፤ በዚያን ጊዜ ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፡ ወይም፦ ከዚያ አለ፡ ቢላችሁ አትመኑ፤
24፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።”
25፤ “እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
26፤ እንግዲህ፦ ‘እነሆ፥ በበረሀ ነው’ ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ ‘እነሆ፥ በእልፍኝ ነው’ ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤
27፤ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤
28፤ በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ።”
29፤ “ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥
30፤ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤
31፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ።”
32፤ “ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤
33፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ።
34፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።
35፤ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።”
36፤ “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም።
Mathew:- ch. 24 nu. 1-36
1. And Jesus went out, and departed from the temple: and his disciples came to him for to shew him the buildings of the temple.
2. And Jesus said unto them, See ye not all these things? verily I say unto you, There shall not be left here one stone upon another, that shall not be thrown down.
3. And as he sat upon the mount of Olives, the disciples came unto him privately, saying, Tell us, when shall these things be? and what shall be the sign of thy coming, and of the end of the world?
4. And Jesus answered and said unto them, Take heed that no man deceive you.
5. For many shall come in my name, saying, I am Christ; and shall deceive many.
6. And ye shall hear of wars and rumours of wars: see that ye be not troubled: for all these things must come to pass, but the end is not yet.
7. For nation shall rise against nation, and kingdom against kingdom: and there shall be famines, and pestilences, and earthquakes, in divers places.
8. All these are the beginning of sorrows.
9. Then shall they deliver you up to be afflicted, and shall kill you: and ye shall be hated of all nations for my name’s sake.
10. And then shall many be offended, and shall betray one another, and shall hate one another.
11. And many false prophets shall rise, and shall deceive many.
12. And because iniquity shall abound, the love of many shall wax cold.
13. But he that shall endure unto the end, the same shall be saved.
14. And this gospel of the kingdom shall be preached in all the world for a witness unto all nations; and then shall the end come.
15. When ye therefore shall see the abomination of desolation, spoken of by Daniel the prophet, stand in the holy place, (whoso readeth, let him understand:)
16. Then let them which be in Judaea flee into the mountains:
17. Let him which is on the housetop not come down to take any thing out of his house:
18. Neither let him which is in the field return back to take his clothes.
19. And woe unto them that are with child, and to them that give suck in those days!
20. But pray ye that your flight be not in the winter, neither on the sabbath day:
21. For then shall be great tribulation, such as was not since the beginning of the world to this time, no, nor ever shall be.
22. And except those days should be shortened, there should no flesh be saved: but for the elect’s sake those days shall be shortened.
23. Then if any man shall say unto you, Lo, here is Christ, or there; believe it not.
24. For there shall arise false Christs, and false prophets, and shall shew great signs and wonders; insomuch that, if it were possible, they shall deceive the very elect.
25. Behold, I have told you before.
26. Wherefore if they shall say unto you, Behold, he is in the desert; go not forth: behold, he is in the secret chambers; believe it not.
27. For as the lightning cometh out of the east, and shineth even unto the west; so shall also the coming of the Son of man be.
28. For wheresoever the carcase is, there will the eagles be gathered together.
29. Immediately after the tribulation of those days shall the sun be darkened, and the moon shall not give her light, and the stars shall fall from heaven, and the powers of the heavens shall be shaken:
30. And then shall appear the sign of the Son of man in heaven: and then shall all the tribes of the earth mourn, and they shall see the Son of man coming in the clouds of heaven with power and great glory.
31. And he shall send his angels with a great sound of a trumpet, and they shall gather together his elect from the four winds, from one end of heaven to the other.
32. Now learn a parable of the fig tree; When his branch is yet tender, and putteth forth leaves, ye know that summer is nigh:
33. So likewise ye, when ye shall see all these things, know that it is near, even at the doors.
34. Verily I say unto you, This generation shall not pass, till all these things be fulfilled.
35. Heaven and earth shall pass away, but my words shall not pass away.
36. But of that day and hour knoweth no man, no, not the angels of heaven, but my Father only.
ቅዳሴ / Liturgy
ቅዳሴ አትናቴዎስ
ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም «ደብር» ማለት «ተራራ» ማለት ሲሆን «ዘይት» ማለት ደግሞ «ወይራ» ማለት ነው። በተገናኝ «ደብረ ዘይት» ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የይወራ ተራራ ማለት ይሆናል።
ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው ያለው። ከግርጌው ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ይገኛል። የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ያረፈበት ወይም የድንግል መካነ መቃብር በዚህ ተራራ ግርጌ ይገኛል። ቤተ ፋጌ እና ቢታንያ በኮረብታው ጫፍ እና በምስራቅ ዳገታ ላይ ይገኛሉ። ይህ ተራራ በመፅሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ብዙ ድርጊቶች የተደረጉበት ቦታ ነው። ጌታችን ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ፣ ስለ ዓለም ፍጻሜና ስለ ዳግም ምጽአት በዚህ ተራራ ላይ በትንቢት መልክ ተናገረ (ማቴ.24፥3)። በዚሁ ተራራ ላይ ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ. 24፥50)። በዚሁ ተራራ ላይ ቀን በከታማና በገጠር ሲያስተምር ውሎ ሌሊት የሚያድርበት የኤሌዎን ዋሻ ይገኛል። በኋለኛው ምጽ አቱ በዚሁ ቦታ እንደሚገለጥ ትንቢት ተነግሯል።(ዘካ. 14፥3–5)።
ስያሜው፦ የዓቢይ ጾም እኩሌታ ላይ ያለው ሰንበት በዚህ ተራራ ተጠርቷል። ይህንን ዕለት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዳግም ምጽአት አድርጎ መዝሙሩን ጽፏል። በዚህ ተራራ ላይ «እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት» (ማቴ.24፥3)። ተብሎ እንደተጻፈው ለደቀ መዛሙርቱ የደግም ምጻቱን፣ የዓለምን ፈጻሜ፣ የትንሣኤ ሙታንን፣ ትምህርት በሰፊው ስላስተማረ በዓሉ በተራራው ስም ተሰይሟል።
የደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ
ከዕለታት አንድ ቀን ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ሥነ ሕንፃ በትኩረት እያንዳንዱን ነገር በመመልከት አደነቁ። ጧት በጸሎት ጊዜ ጸሎታቸውን አድረሰው ሲጨርሱ የጧት ፀሐይ አርፎበት ያሸበረቀውን ቤተ መቅደስ ውበቱን አስተውለው ምን ጥበበኛ እንዳሠራው እየተነጋገሩ ጌታችንንም አብሮ እንዲያደንቅ ሲጠብቁ አስደንጋጭ ነገር ተናጋረ። ያ የሚያደንቁት ቤተ መቅደሱ እንደሚፈርስ፤ አያይዞም ከሞት በኋላ ተነሥቶ እንደሚያረግና ነገር ግን ዓለምን ለማሳለፍ ዳግም እንደሚመጣ ወደፊት የሚሆኑ ሚሥጢራትን እና በቤተ መቅደሱና በሕዝቡ ላይ ሊደርስ ያለውን በትነሹ ጥቆመቸው። ይህም ነገር እረፍት ነሳቸውና ወደ ደብረ ዘይት ከተሻገሩ በኋላ በሰፊው እንዲገልጽላቸው ጠየቁት። ጥያቄውም «እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት» (ማቴ.24፥3) የሚል ነው። በዚህ የጥያቄያቸው ክፍል እንደምናየው ጥያቄያቸው ዕለትና ምልክት ነው። ወይም «መቼ» እና «ምን» የሚል ነው። የቤተ መቅደሱ መፍረስ መቼ ይሆናል? የዓለም መጨረሻና የመምጣትህስ ምልክቱ ምንድን ነው? ጌታችንም በቀኙ ያቁመንና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይል በጥያቄያቸው ላይ ብቻ አተኩሮ ሰፊ መልስ ሰጥቷቸዋል።
መቼ ይሆናል ላሉት የመጀመሪያው ጥያቄ «ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም [ሰውም] ቢሆን የሚያውቅ የለም» (ማቴ.24፥.36)። ሲል አጭር መልስ ሲሰጥ።ስለ ሁለተኛው ጥያቄ ስለ ምልክት ጉዳይ ግን መሸከም እስኪያቅታቸው ድረስ አስተምሯቸዋል። በመልሱም ውስጥ ማስጠንቀቂያዎች፣ ምክሮች፣ ማጽናኛዎችና ምሳሌዎች በብዛት ቀርበዋል በተደጋጋሚ ተወስተዋል።
ምልክቶቹ፦
1ኛ/ ሐሰተኞች ክርስቶሶች
ጌታችን በአንደኛ ደረጃ የተናገረው ምልክት በተለያየ ጊዜ በተለያየ ሀገር ብዙ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንደሚነሡ ነው። የጌታ ቃል አይቀርምና ከዚህ ቀደም ብዙ ሰዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ተነሥተው ነበር። ዋናው በዮሐንስ ራእይ ዕራፍ 13 አውሬ ተብሎ የተጠቀሰውና በቅዱስ ጳውሎስ «የዐመፅ ሰው እርሱም የየጥፋት ልጅ» የተባለው ብዙ ጥፋትና መከራ የሚያደርሰው እና በለ 666 መለያ ምልክቱ ሐሳተኛ ክርስቶስ እሲከገለጥ ደረስ መንገድ ጥራጊዎች የሆኑ አለማማጅ ሐሰተኞች ክርስቶሶች ተነሥተዋል። በእውነተኛው ንጉሥ ክርስቶስ ዳግም መምጣት የሚደመሰሰው ሐሳዊ መሲሕ የመጨረሻውና ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ቤተ ክርስቲያንን የሚወጋ የታላቁ መከራ ፈጻሚና አስፈጻሚ ይሆናል። ለዚህ ነው መድኃኒታችን እስኪመጣ ድረስ እናዳንሰናከል አስቀድሞ «ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ … በዚያን ጊዜ ማንም፦ እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም፦ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ» (ቁጥ. 5 እና 23) ሲል ያስጠነቀቀን።
በሀገራችንም በኢትዮጵያ በአፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንገሥት እኔ ክርስቶስ ነኝ የሚል ሐሳዊ/ሐሰተኛ ክርስቶስ ተነሥቶ እንደነበር በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቧል። ይህ በሀገራችን ተንሥቶ የነበረው ሐሳዊ ክርስቶስ ልክ እንደ እውነተኛው ክርስቶስ 12 ሐዋርያት፣ 72 አርድእትና 36 ቅዱሳት አንስት አስከትሎ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያለ ሲንቀሳቀስ ንጉሡ አስቀርበው አንተ ማን ነህ? ቢሉት በድፍረት እኔ ክርስቶስ ነኝ አላቸው። ንጉሡም ክርስቶስማ ከደንግል ማርያም ተወልዶ አስተምሮ፣ ተሰቅሎ፣ ዓለምን አድኖ ከሞት ተንሥቶ ዐርጓል ዳግም ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል አንተ ግን ማነህ? ቢሉት አዎ ትክክል ነው። ከዚህ ቀደም ከቤተ እሥራኤል ከምትሆን ከድንግል ማርያም ተወልጀ፣ አስተምሬ ተሰቅየ ሙቼ ተነሥቼ ዐርጌ ነበር፤ አሁን ድግሞ ጥቁሮች አፍርካውያን ባይታወር አደረገን እንዳይሉኝ ከእናቴ ከድንግል መርዐተ ወንጌል ለጥቁሮቹ ዳግም ተወልጀ ነው አላቸው። ንጉሡም ሰይጣን በሰው እያደረ እንዴት ይጫወታል ብለው በሰይፍ አስቀጡት ተካታዮቹም ተበተኑ ይባላል።
2ኛ/ ጦርነት
ጦርነት ዱሮም ነበረ። የዚህ ዘመን ጦርነት ግን የበዛና በብዙ ሀገራት የሚካሄድ ነው፣ የዱሮ ጦርነት ሴቶችን፣ አቅመ ደካማ ሺማግሌዎችንና ሕፃናትን ለእልቂት የማያጋልጥ ነበር። የዘመናችን ጦርነት ግን ማንንም የማይለይ ለማንም የማይራራ ሁሉን የሚደፈጥጥ የሁሉን ደም የሚያፈስ አስቃቂነቱ ከመግለጫ ቋንቋ በላይ ሆኖ ይታያል። ይህንንምም ጌታችን የዳግም ምጽ አቱን ምልክት ለጠየቁት ለደቀ መዛሙርቱ ሁለተኛ ምልክት አድርጎ «ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና» (ቁጥማቴ .6-7) ሲል ተናግሮታል።
3ኛ/ ረሀብ
የረሀብ ወሬ ወደ ሌላ ሀገር መሄድ ሳያስፈልገን በገዛ ሀገራችን የምናየው የምንዳሳሰው ያለው ለመርዳት የሌለው ለጸሎት የሚሮጥባት ሀገራችን ኢትዮጵያ አለች። ይህም ሰው ሰራሽ ችግር ለጠላቶቻችን ማሣለቂያ አድርጎን ይኖራል። በተለው የተፈጥሮ ችግር ሳያጋጥማት በሰው ሰራሽ ችግር 8 000 000 ሕዝብ ለአስቸኳ ምግብ ርዳታ የተጋለጠበት ሁኔታ ያሳዝናል። ይህም ዓይነት በጥልና በተንኮል በጭካኔ ሰዎች የሚፈጥሩት ችግር የምጽአት ሦስተኛ ምልክት ሆኖ በጌታችን ለደቀ መዛሙርት ተነግሯል «ረሀብም ቸነፈርም በልዩ ልዩ ሥፍራ ይሆናል» (ማቴ. 24፥7) ተብሎ እንደተጻፈ።
4ኛ/ የምድር መንቀጥቀጥ
የመሬት መንቀጥቀጥ ባለፉት ዓመታት በርካታ ጉዳት በተለያዩ ሀገሮች እንዳደረሰ የሚዘንጋ አይደለም። በ1999፣ ጀምሮ እስከ ዛሬ በተለያዩ ሀገሮች በተለያየ ጊዜ የበዙዎችን ሕይወት የቀጠፈ አያሌዎችን ቤት ንብረት አልባ ያደረገ የመሬት መቀጥቀጥ ተከሥቷል። በሄይቲ፣ በታይዋን፣ በቱርክ፣ በፊልፕንስ፣ ወዘተ ተከሥቷል። ይህም ለደቀ መዛሙርቱ የዓለም ፍጻሜ ምልክት የማግኘት ጥያቄ የተሰጠው «የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል» (ማቴ. 24፥7) ተብሎ በጌታ የዓለም ፍጻሜ ምልክት ተደርጎ የተነገረው ቃል አይቀርምና እየሆነ ነው።
5ኛ/ የክርስቲያኖች መከራ
የክርስቲያኖች መከራ እየጀመረ ይመስላል። ሰይጣን ኢቴስቶችን፣ እስላሞችንና አይሁድን በመጠቀም በክርስቲያኖች ላይ ከምን ጊዜውም በላይ ችግር መፍጠር የቸመረበት ጊዜ ነው። በአውሮፓ የክርስቲያኖች ጥያቄ ቶሎ የማይመልስ የቤተ ክርስቲያንን ጥያቄ ለማስተናገድም መንግስታዊ መሥሪያ ቤቶች ፈቃደኛነታችውን እያጡና ይህንን ወንጀላቸውን ለመሸፈንም በሕግ አንቀጽ እየፈጠሩለት ይታያሉ። «በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ» (ማቴ. 24 ቁጥ.9)። ተብሎ እንደተጻፈው ሃይማኖተኛነት እንደ ኋላ ቀርነት ከሐዲነት እንደተራማጂነትና ሥልጡንነት የሚታይበት ዘመን ላይ እንዳለን ግልጽ ነው። ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ አመለካከት ክርስቲያኖችን ወደ ማግለልና ወደ መወንጀል የሚያድግ መሆኑ ከሚታዩት ፍንጮች መረዳት ይቻላል።
በእንዲህ አይነት የመከራ ዘመን የክርስቶስ ተቃዋሚዎች በክርስቲያኖች ላይ ከሚያመጡት መከራ የበለጠ የክርስቲያኖች እርስ በእርስ መከዳዳት ጭንቁን ያከፋዋል መከራውን መራራ ያደርገዋል «በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ» (ማቴ.24፥10) ተብሎ በጌታ እንደተነገረ ከሐድያኑ ሆነ ብለው በእቅድ በክርስቲያኖች መካከል መከዳዳትን በመፍጠር ለዚህ ነው ክርስቲአኖች ክርስትናን መተው ያለባቸው ፍቅርና መተማመንን ሰላምና ጸጥታን ለማሰፈን ነው ክርስትናን የምንቃወመው እያሉ ድጋፍ ያሰባስባሉ።
6ኛ/ ሐሰተኞች ነቢያት
በዲያብሎስ መንፈስ ምትሐታዊ አሠራርን እያሳዩ አይቻላቸው እንጂ ቢቻላቸው የተመረጡትን ሳይቀር የሚያስቱ ነቢያት ነን የሚሉ ብዙዎች ደፋሮች እንዲመነሡ ጌታችን ስድስተኛ የዳግም ምጽአቱ ምልክት አድርጎ ጠቅሷቸዋል። በአሁኑ ዘመን በሀገራችንም ነቢያት ነን የሚሉ አጭበርባሪዎች እንደ አሸን ፍልተዋል።
እነዚምህም በነቢያ ኤልያስ፣ በነቢዩ ኤልሣዕ ስም እያጭበረበሩና እየዋሹ በምትሐታዊ አሠርራር የሚያስቱ ሐሰተኞች እንደሚነሱ ሌላው የዳግም ምጽአቱ ምልክት ሆኖ «ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ …ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ … እንግዲህ፦ እነሆ፥ በበረሀ ነው ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ እነሆ፥ በእልፍኝ ነው ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤ » (ማቴ 24 ቁጥ.11፥ 24 እና 26) ተብሎ በጥብቅ ተነግሯል። እንግዲህ በዘመናችን በሀገራችን ሆነ በሌላው ዓለም በነቢይነትና በሰባኪነት ስም የሚደረገውን የንግድና የርኩሰት እንቅስቃሴ በማስተዋል መከታተልና መጠበቅ ያስፈልጋል።
7ኛ/ የፍቅር ማጥፋት
ሌላውና አሳዛኙ ጉዳይ የፍቅር መቀዝቀዝ ነው። ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው። የሰው ልጅ ፍቅርን ማጥፋት እና ማጣት የሌለበት ሀብቱ ነው። አሁንም «ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች» (ማቴ.24፥12) የሚለው ትንቢት እንዳይፈጸምብን ፍቅርን መንከባከብ፣ ማልማትና ማስፈት ይገባል። ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው። ፍቅር የመልካምና በጎ ንገር ሁሉ መገኛና ምንጭ ነው።
8ኛ/ የወንጌል መዳረስ
የወንጌል ለዓለም መዳረስ ለደቀ መዛሙርቱ የዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ሁነው ከተሰጡት አንዱ ነው። በፍርዳ ቀን በመጫረሻው ጊዜ በክርስቶስ አምኖ እና እምነቱን በሥራ ግልጾ ስለመኖር ሲጠየቅ አልሰማሁም አላየሁም አላወኩም የሚል አያመልጥም «ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል» (ማቴ. 24፥ 14) ተብሎ እንደተነገረው በሁሉም ቤት ወንጌል ይሰበካል ከሁሉም ዘንድ ይገኛል።
የምጽአቱ ምሳሌዎች
ፍጥነቱ፦ ፈጥነቱ እንደ መብረቅ ነው። «መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል» (ማቴ 24፥ 27):: ተብሏልና።
ቀኑ አለመታዎቁ፦ እንደ ሌባ ነው። ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር … የሰው ልጅም በማታስቡበት ሰዓት ይመጣል (ቁጥ. 43-44)።
ለታሪካዊ ማስገንዘቢያ የኖህ ዘመንም እንደዚሁ ባልታሰበ ሠዓት እንደሚመጣ ማስገንዚያ ሆኖ በጌታችን ቀርቧል። (ከቁጥ. 37-39)።
ወቅታዊ መልእክቱ
ተጠንቀቁ፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ (ቁጥ.4)።
ንቁ፦ጌታችሁ በምን ሠዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ (ቁጥ. 42)
ተማሩ እወቁ፦ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ [ከላይ የተናገራቸውን ምልክቶች ሁሉ] ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ (ቁጥ. 33)።
አትደንግጡ፦ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ (6)
ትጉና ጸልዩ፦ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ (20)
ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፦ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።(44)።
ጽኑ፦ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል (ቁጥ.13)።
እነዚህን ሁሉ ምክሮች፣ ማስጠንቀቂያዎችና ማፅናኛዎች በአእምሮ ጽላት ቀርፆ በማስተዋል በሃይማኖት እና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ጸንቶ የኖረ የሕይወትን ቃል ሰምቶ የክብር፣የድልና የጽድቅ አክሊልን ተሸልሞ በዘላለማዊ ደስታ ይኖራል።
ሦስተኛ የሰው ዘር የጋራ ልደት እና ዕድገት
ከዚህ ሁሉ በኋላ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘላት ዓለም ወደ ፍጻሜዋ ታመራለች፣ ጣዕሟ፣ ለዛዋ ሁሉ ይሟጠጣል፣ ፍጻሜ ዓለም ይሆናል፡፡ ምድር ከመሠረቷ ትናጋለች፣ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ከዋክብትም እንደ ቃርያ ፍሬ ከሰማይ ይረግፋሉ፡፡ (መዝ. 12፥ 2፤ ኢሳ. 13፥ 6-13፤ ኢዩ. 2፥ 10-11፣ 30-32፤ ማቴ. 24፥ 29-41፤ ራዕይ 6፥12-17)፡፡
በታላላቅ ድንጋዮች የታተሙ መቃብሮች በውስጣቸው የያዙአቸውን ሙታን ይሰጣሉ፣ የሙታን ሥጋ ከረጅም የእንቅልፍ ዓለም ይባንንና ሁሉም በአንድ ቀን ከመቃብር ተወልደው በአንድ ቀን አድገው ወደ ፍርድ አደባባይ ይሰበሰባሉ፣ ታላቁ ዘንዶ ለብዙዎች ስሕተት ምክንያት የሆነው ዲያብሎስ ከነሠራዊቱ ለዘላለም በማይፈታ በእሳት ሰንሰለት ታስሮ ወደ ገሃነመ እሳት ይጣላል፡፡ ፊተኞቹ ሰማይና ምድር ከፍጡራን ፊት እንደወረቀት ተጠቅልለው ያልፋሉ፣ ስፍራም አይገኝላቸውም ለዘለአለምም ያልፋሉ፡፡ (ኢሳ. 13፥ 6-13፤ መክ. 12፥ 17፤ 1ኛ ተሰ. 4፥ 13-18፤ 2ኛ ጴጥ. 3፥ 10)፡፡
በበጉ ደም የተዋጁና ሃይማኖታቸውን የጠበቁ ታማኝ የክርስቶስ ልጆች ገናናውንና ታላቁን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ሊቀበሉ በታላቅ ክብር በደመና ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ፡፡ የአብ ልጅ የድንግል ማርያም ልጅ የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስም በታላቅና እጅግ አስፈሪ በሆነ መለኮታዊ ግርማ የብዙ ብዙ በሚሆኑ እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ታጅቦ ይመጣል፡፡ (ዘካ. 14፥ 6፤ ማቴ. 25፥ 31፤ 1ኛ ተሰ. 4፥ 16)፡፡
በዚያን ጊዜ በፊቱ ችሎ የሚቆም ማን ይሆን? (ኢዩ. 2፥ 11) አመጣጡም እንደቀደመው ከሐና ወደ ቀያፋ ከዚያም ወደ ጲላጦስ አደባባይ እያንገላቱ ሲወስዱት ዝም እንዳለ በዚህ ዓይነት አመጣጥ አይደለም፡፡ የሚመጣው በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ መለኮታዊ ግርማና ክብር ነው፡፡ (መዝ. 49፥ 2)፡፡ መጥቶም ዝም አይልም እሳት በፊቱ ይነዳል ኃጥአንን ከፊቱ ጠራርጎ ወደ ገሃነመ እሳት የሚጨምር ጥቅል አውሎ ነፋስም አለ፡፡ (ማቴ. 24፥ 30፤ ራዕይ 1፥ 7)።
እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥአንን በግራው ለይቶ ያቆማቸዋል፡፡ በቀኙ ያሉትን “እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ ወደ አባታችሁ መንግስተ ሰማያት ግቡ፡፡” ብሎ ለዘለዓለም ሕይወት ይጠራቸዋል፡፡ በግራው ያሉትን ደግሞ እጅግ በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ የቁጣ ቃል “እናን ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” ይላቸዋል፡፡
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ትወርዳለች ማለት ለምእመናን ትሰጣለች፡፡ ምእመናንም ርስት መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉ ብርሃን ለብሰው ብርሃንን ተጎናጽፈው ለዘለዓለም በደስታ ይኖራሉ፡፡ (ማቴ. 25፥ 31-46፤ ራዕይ 21፥ 1-2)፡፡
ኦርቶዶክሳውያን! ነቢዩ ኤርምያስ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርስዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ” (ት.ኤር. 6፣ 16)፡፡ በማለት እንደተናገረው በቀደመችው በመልካሚቱ የሕይወትና የጽድቅ መንገድ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነታችን እስከ መጨረሻው ድረስ ጸንተን ልንኖር ይገባል፡፡
ማጠቃለያ
ደብረ ዘይት እንግዲህ ተጽፎና ተተርጉሞ የማያልቅ ሰፊ፣ ጥልቅና ምጡቅ ትምህርትን የያዘ በዓል ነው። በደቀ መዛሙርቱ ሁለት ብቻ ጥያቄዎች ተነሥቶ ያስተማረው የዕለተ ምጽአቱ ነገር በአጭር ጽሑፍ የሚካተት ስላልሆነ በሀገር ቤት የታላቋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ኦርቶዶክሳውያን ይህንን በዓል በየዓመቱ እንዴት እንደሚያዘክሩት በማሳየት እናቆየዋለን።
በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ይህ በዓል በሀብታሙም በድሀውም በትልቁም በትንሹም ዘንድ በበጎ ሥራ በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ተከብሮና ታስቦ ይውላል። ሕዝበ ክርስቲያኑ ያለውም የሌለውም ቤት ያፈራውን ምግብ ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣና ከመንፈሳዊ አገልግሎት በኋላ አስቀድሞ ድሆችን በመጎብኘት፣ በመመገብና በማጽናናት ከደሆች የተረፈውን እርስ በእርስ በመገባበዝ፣ የተጣላ በማስታረቅ በቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ከዋርካውና ከፅዱ ሥር አርፎ ይውላል።
ክርስቲያኑ ሕዝብ ይህንን የሚያደርግበትን ምክንያትም ሲገልጽ ዓለምን ለማሳለፍ ጌታችን የሚመጣ በዚህ ዕለት ስለሆ ሲመጣም እንዲህ ያለ ደግ ሥራ የሠሩትን ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ብሎ መንግሥቱን እንዲያወርሰን ነው ይላሉ።
ምእመናኑ ለምን ይህን እንደሚያደርጉ ሲጠየቁ የሚሰጡት ሁለተኛው መልስ ደግሞ የሞቱት ነፍሳት በዚህ ዕለት ይሰበሰባሉ ወይም ይመጣሉ ዘመዳቸው የሆነ ጥሬ ወይም እንጀራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስዶ ለነዳያን የሰጠ እንደሆነ ደስ ይላቸዋል። የሞተ ዘመድ ያለው አንድ ሰው በደብረ ዘይት ዕለት ጥሬ ወይም እንጀራ ወደ ቤተ ክርስቲያን አምጥቶ ካልመጸወተ የዘመዱ ነፍስ መጥታ የኔስ ዘመዶች አልቀዋል ብላ አዝና ትመለሳለች ይላሉ። ምስጢሩ ከላይኛው አይርቅም።
ይህ ደብረ ዘይት ወይም አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት ሌሎች ስያሜዎችም አሉት። በተጨማሪ ዳግም ምጽዐት፣ የፍርድ ቀን፣ የጌታ ቀን፣ ሕልቀተ/ሕልፈተ ዓለም፣ ዕለተ ፍዳ፣ ዕለተ ደይን ዳግመኛ ልደት ትንሣኤ ዘጉባዔ በመባል በመጽሐፍ ቅዱስና በቅዱስ ያረድ ድርሰቶች ይጠራል።
የእግዚአብሔር ጥሪ ሁሉም የአዳም ዘር መንግሥቱን እንዲወርሱ ቢሆንም የሰይጣንን ወጥመድና አሸከላ ሁሉ አልፈው፤ በሐሰተኞች ክርስቶሶችና በሐሰተኞች ነቢያት ምትሐታዊ ተአምራት ሳይሳቡና ሳይሰናከሉ እስከ መጨረሻው ጽንተው በዚያ በዳግመኛ ልደት እና የመጨረሻ የዋጋ ቀን በጌታቸው ቀኝ የሚቁሙ የታደሉ ናቸው።
እንግዲህ እኛን በቀኙ ያቁመን ዘንድ የአባቴ ቡሩካን ኑ ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ የሚለውን የሕይወት ቃሉንም ያሰማን ዘንድ የአምላካችን የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።
ስለ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እመቤታችን ብሎ ልጇ መድኃኔዓለም በዚያ የሚያስፈራ ቀን ይራራልን። በዕለተ ዐርብ የፈሰሰው ክቡር ደሙ ከትንሣዔ ዘጉባዔ ክብር የሚለየንን ነውራችንን ይሸፈንልን አሜን።
ምንጭ ፦ https://eotcnor.no/