Loading

የዐቢይ ጾም ሶስተኛው ሳምንት – ምኵራብ / Temple

የዐቢይ ጾም ሶስተኛው ሳምንት – ምኵራብ / Temple

This post is only available in Amharic.

በዕለቱ የሚነበቡት መልዕክታት

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆላስያስ ሰዎች:- ም. 2 ቊ. 16-ፍ.ም / St Paul’s letter to the people of Colossians:- ch. 2 nu. 16-end

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆላስያስ ሰዎች:- ም. 2 ቊ. 16-ፍ.ም

16፤ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።

17፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።

18፤ ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ።

19፤ እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል።

20-21፤ ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥

22፤ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት፦ “አትያዝ”፥ “አትቅመስ”፥ “አትንካ”፡ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና።

23፤ ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም።

English

St Paul’s letter to the people of Colossians:- ch. 2 nu. 16-end

16. Let no man therefore judge you in meat, or in drink, or in respect of an holyday, or of the new moon, or of the sabbath days:

17. Which are a shadow of things to come; but the body is of Christ.

18. Let no man beguile you of your reward in a voluntary humility and worshipping of angels, intruding into those things which he hath not seen, vainly puffed up by his fleshly mind,

19. And not holding the Head, from which all the body by joints and bands having nourishment ministered, and knit together, increaseth with the increase of God.

20. Wherefore if ye be dead with Christ from the rudiments of the world, why, as though living in the world, are ye subject to ordinances,

21. (Touch not; taste not; handle not;

22. Which all are to perish with the using;) after the commandments and doctrines of men?

23. Which things have indeed a shew of wisdom in will worship, and humility, and neglecting of the body; not in any honour to the satisfying of the flesh.

የያዕቆብ መልዕክት:- ም. 2 ቊ. 14-ፍ.ም / St James’s letter:- ch. 2 nu. 14-end

የያዕቆብ መልዕክት:- ም. 2 ቊ. 14-ፍ.ም

14፤ ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?

15፤ ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥

16፤ ከእናንተ አንዱም፦ “በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም፡” ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

17፤ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።

18፤ ነገር ግን አንድ ሰው፦ “አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ፡” ይላል።

19፤ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።

20፤ አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?

21፤ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

22፤ እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?

23፤ መጽሐፍም፦ “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፡” ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።

24፤ ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ።

25፤ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?

26፤ ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

English

St James’s letter:- ch. 2 nu. 14-end

14. What doth it profit, my brethren, though a man say he hath faith, and have not works? can faith save him?

15. If a brother or sister be naked, and destitute of daily food,

16. And one of you say unto them, Depart in peace, be ye warmed and filled; notwithstanding ye give them not those things which are needful to the body; what doth it profit?

17. Even so faith, if it hath not works, is dead, being alone.

18. Yea, a man may say, Thou hast faith, and I have works: shew me thy faith without thy works, and I will shew thee my faith by my works.

19. Thou believest that there is one God; thou doest well: the devils also believe, and tremble.

20. But wilt thou know, O vain man, that faith without works is dead?

21. Was not Abraham our father justified by works, when he had offered Isaac his son upon the altar?

22. Seest thou how faith wrought with his works, and by works was faith made perfect?

23. And the scripture was fulfilled which saith, Abraham believed God, and it was imputed unto him for righteousness: and he was called the Friend of God.

24. Ye see then how that by works a man is justified, and not by faith only.

25. Likewise also was not Rahab the harlot justified by works, when she had received the messengers, and had sent them out another way?

26. For as the body without the spirit is dead, so faith without works is dead also.

የሐዋርያት ሥራ:- ም. 10 ቊ. 1-9 / Acts of The Apostles:- ch. 10 nu. 10-9

የሐዋርያት ሥራ:- ም. 10 ቊ. 1-9

1፤ በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ።

2፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።

3፤ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፦ “ቆርኔሌዎስ ሆይ፡” የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።

4፤ እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ፦ “ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው?” አለ። መልአኩም አለው፦ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።

5፤ አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ።

6፤ እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።”

7፤ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሎዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥

8፤ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው።

9፤ እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ።

English

Acts of The Apostles:- ch. 10 nu. 10-9

1. There was a certain man in Caesarea called Cornelius, a centurion of the band called the Italian band,

2. A devout man, and one that feared God with all his house, which gave much alms to the people, and prayed to God alway.

3. He saw in a vision evidently about the ninth hour of the day an angel of God coming in to him, and saying unto him, Cornelius.

4. And when he looked on him, he was afraid, and said, What is it, Lord? And he said unto him, Thy prayers and thine alms are come up for a memorial before God.

5. And now send men to Joppa, and call for one Simon, whose surname is Peter:

6. He lodgeth with one Simon a tanner, whose house is by the sea side: he shall tell thee what thou oughtest to do.

7. And when the angel which spake unto Cornelius was departed, he called two of his household servants, and a devout soldier of them that waited on him continually;

8. And when he had declared all these things unto them, he sent them to Joppa.

9. On the morrow, as they went on their journey, and drew nigh unto the city, Peter went up upon the housetop to pray about the sixth hour.

ምስባክ

እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ።
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ።
ወቀፃዕክዋ በጾም ለነፍስየ።
መዝሙር:- ፷፰: ፱-፲

የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት።
መዝሙር:- 69:9-10

For the zeal of thine house hath eaten me up;
and the reproaches of them that reproached thee are fallen upon me.
I chastened my soul with fasting.
Psalms:- 69:9-10

ወንጌል / Gospel

ዮሐንስ:- ም. ፪(2) ቊ. ፲፪(12)-ፍ.ም / John:- ch. 2 nu. 12-end

ወንጌል:- ዮሐንስ:- ም. ፪(2) ቊ. ፲፪(12)-ፍ.ም

12፤ ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።

13፤ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።

14፤ በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤

15፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥

16፤ ርግብ ሻጪዎችንም፦ “ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት፡” አላቸው።

17፤ ደቀ መዛሙርቱም፦ “የቤትህ ቅናት ይበላኛል፡” ተብሎ እንደ ተጻፈ፡ አሰቡ።

18፤ ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ “ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት።

19፤ ኢየሱስም መልሶ፦ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ፡” አላቸው።

20፤ ስለዚህ አይሁድ፦ “ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን?” አሉት።

21፤ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።

22፤ ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

23፤ በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤

24-25፤ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።

English

Gospel:- John:- ch. 2 nu. 12-end

12. After this he went down to Capernaum, he, and his mother, and his brethren, and his disciples: and they continued there not many days.

13. And the Jews’ passover was at hand, and Jesus went up to Jerusalem,

14. And found in the temple those that sold oxen and sheep and doves, and the changers of money sitting:

15. And when he had made a scourge of small cords, he drove them all out of the temple, and the sheep, and the oxen; and poured out the changers’ money, and overthrew the tables;

16. And said unto them that sold doves, Take these things hence; make not my Father’s house an house of merchandise.

17. And his disciples remembered that it was written, The zeal of thine house hath eaten me up.

18. Then answered the Jews and said unto him, What sign shewest thou unto us, seeing that thou doest these things?

19. Jesus answered and said unto them, Destroy this temple, and in three days I will raise it up.

20. Then said the Jews, Forty and six years was this temple in building, and wilt thou rear it up in three days?

21. But he spake of the temple of his body.

22. When therefore he was risen from the dead, his disciples remembered that he had said this unto them; and they believed the scripture, and the word which Jesus had said.

23. Now when he was in Jerusalem at the passover, in the feast day, many believed in his name, when they saw the miracles which he did.

24. But Jesus did not commit himself unto them, because he knew all men,

25. And needed not that any should testify of man: for he knew what was in man.

ቅዳሴ / Liturgy

ቅዳሴ እግዚእነ

ሦስተኛው ሰንበት “ምኲራብ” ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት “ቦአ ኢየሱስ ምኲራበ አይሁድ” ነው፣ ምኩራብ ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ህንፃ ማለት ነው፣ ከዚህም የተነሣ “የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ” ማለት ይሆናል፣ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያነ ሥጋን በትምህርቱ፣ ድውያነ ነፍስን በታምራቱ ሲፈውስ በምኩራብ ዮሐንስ ምዕራፍ 2 ቁጥር 12 እየተገኘ የፈጸመውን የማዳን ሥራ በኀሊና እያሳሰበ የሚያስተምር ሦስተኛ ሳምንት ነው፡፡

ኢየሱስ በሰንበት ቀን ወደ አይሁድ ምኲራብ ገባ እያለ ማስተማሩን እየጠቃቀሰና እያነሳሳ ስለሚዘምር ይህን ሰንበት ለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኲራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኲራብ የሚሸጡ፣ የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ፣ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ሆኖ ስለተሰጠ ነው፣ የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ቁጥር 12-13 ተጠቅሷል፡፡

ቆላስያስ ምዕራፍ 2 ቁጥር 16-23 “እንግዲህ በመብል ወይ በመጠጥ ወይም ስለ በዓል፣ ወይም ስለ ወር መባቻ፣ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፣ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፣ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው፣ ትህትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፣ ባላየውም ያለፈቃድ እየገባ፣ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤ እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፣ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሠሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፣ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል፡፡

ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፣ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት “አትያዝ አትቅመስ፣ አትንካ” ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም ሁሉ እንደምትኖሩ ስለምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና፣ ይህ እንደገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፣ ነገር ግን”ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም” ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል፣
ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እህት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፣ ከእናንተ አንዱም በደህና ሂዱ፣ እሳት ሙቁ፣ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጧቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚሁም “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ነገር ግን አንድ ሰው አንተ እምነት አለህ፣ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፣ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል፡፡

በእግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፣ አንተ ከንቱ ሰው፣ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችን አብርሐም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፣ በሥራም እምነት እንደተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም አብርሐምም እግዚአብሔርን አመነ፣ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ያለው ተፈፀመ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፣ “ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲፀድቅ ታያላችሁ”፣ እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን? “ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ፣ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው”

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 ቁጥር 1-9 “በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነው ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፣ እርሱም ፅድቅና ከነቤተሰቡ እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ፣ ለህዝብም ብዙ ምፅዋት የሚያደርግ፣ዘወትር  ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፣ እግዚአብሔር መልአክም በራእይ ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት  “ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው” እርሱም ትኩር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ “ጌታ ሆይ ምንድን ነው? አለ፣ መልአኩም  “ጸሎትህና ምፅዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን ዐረጓል” አለው፣ አሁንም “ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ፣ እርሱ ቤቱ በባህር አጠገብ ባለው በቁርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጧል፣ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል፣ የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ ከሎሌዎቹ ሁለቱን፣ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፣ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው፣ እነርሱም በነጋታው ሲሄዱ፣ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፣ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ፣ መዝሙር ምዕራፍ 68 ቁጥር 9-10 የቤትህ ቅንዓት በልቶኛልና፣ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና ሰውነቴን በጾም አደከምኳት፣ ስድብንም ሆነብኝ”፡፡

ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ “ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ”፣ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፣ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፣  ዮሐንስ ምዕራፍ 2 ቁጥር 12 -25 ወደ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን፣ ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፣ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፣ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፣ ርግብ ሻጪዎችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፣ “የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት” አላቸው፣ ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅናት ይበላኛል” ተብሎ እንደተፃፈ አሰቡ፡፡

ስለዚህ አይሁድ መልሰው ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት፣ ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው” ስለዚህ  አይሁድ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፣ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት፣ እርሱ ግን “ስለ ሰውነቱ ቤተመቅደስ ይል ነበር” ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ፡፡

በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፣ “ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፣ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና”

“ወስብሐት ለእግዚአብሔር”

ምንጭ ዮሐንስ ንስሐ የቴሌግራም ግሩፕ
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

Share this post

Current News

1 min read

በደብራችን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ።

በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት ኅዳር 21/2018 ዓ/ም በለንደን ጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀብለዋል።

Current News

1 min read

ዜና ቤተክርስቲያን

በዛሬው ዕለት በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንየመጭውን የጻድቁ አባታችንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት ለሚደረገው ዝግጅት በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ጥረት የህንጻ ግዢ የገቢ አሰባሳቢክፍሉ በደብሩ ያሉትን የአገልግሎት ክፍሎች በጋራ ሊያሳካ ስለሚችለው ውይይት አድርጏል ለዚሁም ይረዳው ዘንድ በዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቅም ስልጠና ተሰጥቷል::

Current News

1 min read

ዜና ቤተክርስቲያን

በትናንትናው ዕለት ማለትም በ17/12/2017 ዓም (August 23/2025) በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አንድ አዲስ ነገር ተፈፅሟል ይኸውም ጀማል የተባለ ከእስልምና ወደ ክርስትና በመምጣት መስረታዊ የክርስትና ትምህርቱን በተገቢ መንገድ አጠናቅቆ የሥላሴ ልጅነቱን አግኝቷል ትምህርቱንም የሰጠው ዲያቆን ዘማርያም ሲሆን በደብራችንም ተጨማሪ ክትትል በማድረግ እነሆ ተከናውኗል እግዚአብሔር ይመስገን::