Loading

በአውሮፓ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ “የተክልዬ ተጓዦች” በሚል ስያሜ በኢንግላንድ ከስቶክ ኦን ትሬንት ወደ ሊቨርፑል በሚጓዙ ምእመናን ተጀመረ !

በአውሮፓ የመጀመሪያው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ “የተክልዬ ተጓዦች” በሚል ስያሜ በኢንግላንድ ከስቶክ ኦን ትሬንት ወደ ሊቨርፑል በሚጓዙ ምእመናን ተጀመረ !

This post is only available in Amharic.

ቀደምት አባቶችን በመዘከር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዋወቅና የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ሐዋርያዊ ጉዞ ምክንያት በማድረግ ታላቋ ብሪታንያ በስቶክ ኦን ትሬንት ከተማ የሚገኙ የቅዱስ ሩፋኤል ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ መንፈሳዊ ማኅበር አባላት የፊታችን ቅዳሜ በሊቨርፑል ከአቡነ ተክለሃይማኖት የሚከበረውን የጻድቁን የዕረፍት በዓል ምክንያት በማድረግ በአውሮፓ አህጉር የመጀመሪያውን 18 ሰዓታት የሚወስደውን የእግር ጉዞ በዛሬው ዕለት ጀምረዋል።

የእግር ጉዞው ነገ ዓርብ ከቀትር በኃላ ሊቨርፑል በመግባት እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ምእመናኑ በሚያልፉባቸው ከተሞች የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ሐዋርያዊ ጉዞ በማሰብ በየከተማው ለሚገኙ የሀገሪቱ ነዋሪዎች የጻድቁን ሕይወትና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማስተዋወቅ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን ጉዞ የሚያደርጉ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ምእመናን በዓይነቱ ልዩ የሆነውን እና ለበጎ ዓላማ የሚካሄደውን ይህንን መንፈሳዊ የእግር ጉዞ በማበረታታት ላይ እንደሚገኙ ነው የተጠቆመው።

ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ለንደን)

ይህንን በፌስቡክ ይመልከቱ

Share this post

Current News

1 min read

በደብራችን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ።

በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የግብረ ድቁና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አምስት ደቀመዛሙርት ኅዳር 21/2018 ዓ/ም በለንደን ጽርሐ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀብለዋል።

Current News

1 min read

ዜና ቤተክርስቲያን

በዛሬው ዕለት በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንየመጭውን የጻድቁ አባታችንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በማስመልከት ለሚደረገው ዝግጅት በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚደረገው ጥረት የህንጻ ግዢ የገቢ አሰባሳቢክፍሉ በደብሩ ያሉትን የአገልግሎት ክፍሎች በጋራ ሊያሳካ ስለሚችለው ውይይት አድርጏል ለዚሁም ይረዳው ዘንድ በዘመኑ ቴክኖሎጂን በመጠቅም ስልጠና ተሰጥቷል::

Current News

1 min read

ዜና ቤተክርስቲያን

በትናንትናው ዕለት ማለትም በ17/12/2017 ዓም (August 23/2025) በሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አንድ አዲስ ነገር ተፈፅሟል ይኸውም ጀማል የተባለ ከእስልምና ወደ ክርስትና በመምጣት መስረታዊ የክርስትና ትምህርቱን በተገቢ መንገድ አጠናቅቆ የሥላሴ ልጅነቱን አግኝቷል ትምህርቱንም የሰጠው ዲያቆን ዘማርያም ሲሆን በደብራችንም ተጨማሪ ክትትል በማድረግ እነሆ ተከናውኗል እግዚአብሔር ይመስገን::