Liverpool M.K Abune Teklehaymanot Church
Ethiopian Orthodox Tewahdo Church In Liverpool

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት – ገብር ኄር / Faithful Servant

በጎ አገልጋይ ለጌታው ታምኝ እንደመሆኑ ‹‹ገብር ኄር›› ይባላል፡፡ ይህም ስያሜ ለዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት እንደተሰጠ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ይገልጻል፡፡ የስያሜው መነሻ የሚገኘው ደግሞ በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው በማቴዎስ ወንጌል ክፍል ነው፡፡ (ማቴ.፳፭፥፲፬-፴)ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ካስተማራቸው

የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት – ደብረ ዘይት / Mount Olives

ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም «ደብር» ማለት «ተራራ» ማለት ሲሆን «ዘይት» ማለት ደግሞ «ወይራ» ማለት ነው። በተገናኝ «ደብረ ዘይት» ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የይወራ ተራራ ማለት ይሆናል።ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው

የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት – መፃጒዕ / infirmity

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መፃጒዕ› ይባላል፡፡ ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል ያለ ነው፡፡ መፃጒዕ ደዌ የጸናበት በሽተኛ፣ ሕመምተኛ ማለት ነው፡፡ መፃጒዕ ለ፴፰ ዓመት በአልጋው ላይ ሆኖ ምሕረትን ሲጠባበቅ የኖረ ሰው ነው። ስፍራዋም “ቤተ ሳይዳ” ትባላለች።ቤተ ሣህል (የምሕረት ቤት) ማለት ነው፤ መጠመቂያዋም በሰሎሞን ቤተ

የዐቢይ ጾም ሶስተኛው ሳምንት – ምኵራብ / Temple

ሦስተኛው ሰንበት "ምኲራብ" ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በዚሁ ዕለት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ ሰላሙ ድረስ በዕለተ ሰንበት "ቦአ ኢየሱስ ምኲራበ አይሁድ" ነው፣ ምኩራብ ማለትም ቀጥተኛ ፍችው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ህንፃ ማለት ነው፣ ከዚህም የተነሣ "የአይሁድ ቤተ ጸሎት ወይም ቤተመቅደስ" ማለት ይሆናል፣ ዐቢይ ፍሬ ቃሉ ግን

የብፁዕ  ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ፲፪ኛ ዓመት  በዓለ ሢመት

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲፪ኛ  ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።ዘገባው የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል እና የኢ/ኦ/ተ/ቤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው ::

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለደብራችን ዋና ጸሐፊ ሊቀ ሥዩማን ዳግማዊ ወርቁ የቅስና ሥልጣነ ክህነት ሰጡ!

እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ የደብራችን መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ሊቀ ሥዩማን ዳግማዊ ወርቁ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በብፁዕነታቸው አንብሮተ ዕድ የቅስና ሥልጣነ ክህነትን ተቀብለዋል።የደብራችን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለሊቀ ሥዩማን ቀሲስ ዳግማዊ ወርቁ መልካም የአገልግሎት ዘመንን ይመኛል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ለ312 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ሰጡ፡፡

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ እና ገላን ክፍላተ ከተማ ሥር በሚተዳደረው በዓለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከተለያዩ ገዳማት እና አድባራት ለተውጣጡ 270 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ዲቁና ለ38 ዲያቆናት የቅስና እንዲሁም ለ4 አባቶች የቁምስና ሥልጣነ ክህነት ተሰጥቷል፡፡በዕለቱ ለደቀ መዛሙርቱ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚመቻችሁም

ታላቅ የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ

የነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት መጠናቀቁን አስመልክቶ፤ በዛሬው ዕለት በደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የምስጋና እና የእውቅና መርሐ ግብር አካሂዷል።በመርሐ ግብሩ በዓመቱ የተሠሩት ሥራዎች እና የተገኘው አመርቂ ውጤት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ለብፁዕነታቸው እንዲሁም የአዲስ አበባ ከንቲባ መስተዳደር ላደረጉት

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያን በውግዘት ተለይተው የነበሩትን የዐሥራ ሰባቱ አባቶች ውግዘት ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደም ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ክህነት ውጭ በሆነ መንገድ በራሳቸው ሥልጣንና በይገባናል ስሞታ የኦሮሚያ ሲኖዶስ መሥርተናል በሚል ተልእኮ ሲንቀሳቀሱ ቢቆዮም በይቅርታ መመለሳቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህን ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡በዚህም መሠረት ከመጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ጀምሮ የሦስቱን አባቶችና የሃያዎቹን መነኮሳት ውግዘት ቅዱስ