Liverpool M.K Abune Teklehaymanot Church
Ethiopian Orthodox Tewahdo Church In Liverpool

ሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዩኬና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በማኅበርነት ሰባት ዓመታትን ቆይቷል። በእነዚህ ሰባት ዓመታት ውስጥ ምእመናን የራሳቸው አገልግጋይ እና አጽናኝ ካህን ወይም መምህር ሳይኖሯቸው ከሌሎች ከተሞች በሚመጡ ካህናትና መምህራን በመጽናናት እግዚአብሔርን ዘወትር በማገልገል ቆይተዋል። ከሰባት ዓመታት በኋላ የምእመናኑ ጸሎት ተሰምቶ ልመናቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ  አገልጋይ ካህን ካሉበት እግዚአብሔር ወደዚህ ሥፍራ አመጣቸው። ይህንን ፈቃደ እግዚአብሔር የተመለከቱት በወቅቱ  የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ እንጦንስ አዲስ ከመጡት ካህን ቀሲስ ብርሃኑ ጋር በመነጋገር ቦታውን በቋሚነት እያገለገሉ ምእመናኑን እየባረኩ እና እያጽናኑ በእረኝነት እንዲጠብቁ አደረጉ። በዚህም መሠረት ቅዳሴ ቤቱ ጥር 24 ቀን 2006 ዓ.ም (Feb. 1 2014 GC) በብፁዕ አቡነ እንጦስ ተባረኮ የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ታቦት እንዲገባ የቦታውም ስም መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት እንዲባል ብሎም የካህኑ የማዕረግ ስም ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ብርሃኑ እንዲባል ተደረገ። ከዚች ዕለት ጀምሮ የሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሰፊ የሆነውን መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

እርስዎም ይምጡ ይሳተፉ

 የተለያዩ መርሐ ግብራት ሲኖሩ መጥተው ይሳተፉ ዘንድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች!

መርሐ ግብራችን

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየሁለት ሳምንቱ ቋሚ የቅዳሴ መርሐ ግብር ታካሂዳለች

አኃዛዊ መረጃዎች

የምእመናን (የአባላት) ቁጥር
0
የአገልጋይ ካህናት ቁጥር
0
የሰንበት ተማሪዎች ቁጥር
0
በዓመቱ የተጠመቁ ምእመናን
0

የቤተ ክርስቲያናችን አባል ይሁኑ

በሊቨርፑል እና አካባቢዋ የሚኖሩ ከሆነ የቤተ ክርስቲያናችን ቋሚ አባል በመሆን በየጊዜው በሚካሄዱ መርሐ ግብሮች ላይ እንዲሳተፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች

ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ፈላጊዎች

ቀጣይ መርሐ ግብራት

የቤተ ክርስቲያናችንን ቀጣይ ሙሉ የቅዳሴ አገልግሎት ቀኑን እና ሰዓቱን ለማወቅ እዚህ ላይ ይጫኑ

ወቅታዊ መረጃዎች

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያን በውግዘት ተለይተው የነበሩትን የዐሥራ ሰባቱ አባቶች ውግዘት ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደም ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ክህነት ውጭ በሆነ መንገድ በራሳቸው ሥልጣንና በይገባናል ስሞታ የኦሮሚያ ሲኖዶስ መሥርተናል በሚል ተልእኮ ሲንቀሳቀሱ ቢቆዮም በይቅርታ መመለሳቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህን ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት ከመጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ጀምሮ የሦስቱን አባቶችና የሃያዎቹን መነኮሳት ውግዘት ቅዱስ

ዜና ዕረፍት

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ እንዲሁም የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ባለመቻሉ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል። በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ የኢሜል አድራሻዎን ያስገቡ

የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን !