በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በሰበታ እና ገላን ክፍላተ ከተማ ሥር በሚተዳደረው በዓለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከተለያዩ ገዳማት እና አድባራት ለተውጣጡ 270 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ዲቁና ለ38 ዲያቆናት የቅስና እንዲሁም ለ4 አባቶች የቁምስና ሥልጣነ ክህነት ተሰጥቷል፡፡
በዕለቱ ለደቀ መዛሙርቱ መልእክት ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚመቻችሁም በማይመቻችሁም ሁሉ ድሀ ሀብታም ሳትሉ ሁሉን በአግባቡ እና በሥርዓቱ ማገልገል ይጠበቅባችዋል ብለዋል፡፡
ብፁዕነታቸው አክለውም ይህ ሥልጣን ለማንም ያልተሰጠ ሰማያዊ ሥልጣን ነውና ዛሬ የተሾማችሁ ሁሉ በብርታት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተጋችሁ ሁኑ ሲሉ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ነው፡፡ ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት