የዩኬና አየርላንድ ማህበረ ካህናት ከሀገራችን በህገ-ወጥ መንገድ መውጣቱ የተነገረለትን ረዥም ዓመታት ያስቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያንን ነዋየ ቅዳሳት ከእንግሊዝ ሀገር አስመለሰ።
በርክክቡ ወቅት የተገኙት የዩኬና አየርላንድ ማኀበረ ካህናት ዋና ሰብሳቢ መጋቤ ሥርዓት ቀሲስ ሚካኤል ለቅርሱ መመለስ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን አካላት በማመስገን የዩኬና አየርላንድ ማኀበረ ካህናት በተለይ በዪኬና አየርላንድ በጀመራቸዉ መጠነ ሰፊ ቤተክርስቲያንን የማስተዋወቅ እና ቅርሶቻችንን የማስመለስ እንቅስቃሴ ሁሉም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የወጡ ቅርሶች በእንግሊዝ፣ ጣልያንና ፈረንሳይ በስፋት እንዳሏት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በተያያዘ ዜናም በዕለቱ በተካሄደው በዩኬ የሃይማኖቶች ኀብረት ጉባኤ ላይ ማኀበራችን የተሳተፈ ሲሆን ስለ ዩኬና አየርላንድ ማህበረ ካህናት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልግሉት በዩኬ እና አየርላንድ አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ተደርጓል።
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCYUkIT_TcBYzR12SgxV2YHA
አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡካችንን ይመልከቱ።
https://www.facebook.com/mahibere.kahinatuk.5