ሰላም ይሁን ለሁላችሁም
ይህ ድንግተኛ ክስተት እንደ ኮሚኒቲ አደናግጦን ነበር:: ሆኖም በናንተው ቅንና በጎ ትብብር የእህታች የአስክሬን ሽኝት በተሳካ ሁኔታ እውን ሊሆን ችሏል። ለዚህ ስኬት ህብረተሰቡን ከተለያየ ቦታ በማስተባበር እና ገንዘብ በመሰብሰብ የረዱንን እንደሚከተለው እናቀርባለን:
1- በሊቀ ትጉሃን ብርሃኑ እስተባባሪነት ከሊቨርፑል መካነ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን: ከሊቨርፑል ከኤርትራ ቅዱስ ኡራኤል: ሊድስ መድሃኔ አለም: ሼፌልድ ቅዱስ ሚካኤል በድምሩ £4670.67
2- የማንችስተር ደብረ ሰላም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን £1225
3-በጎፈንድሚ የተስበስበ ከአገልግሎት ክፍያ ውጪ £1973
4-ከለንደን በሳራ በኩል የተገኝ የድሬ ልጆች £1800
5- ከሟች አዜብ ቤት የተገኘ £200
6- የማንችስተር ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን £391.29
7- የስላሴ ማህበረተኞች £200
8- ለእኔ በግል የተሰጠ £110
በድምሩ ባጠቃላይ £10,569.96 ማሰባሰብ ተችሏል
ከዚህ ውስጥ ለአስክሬን ዝግጅትና ወደ ሀገር ቤት እስክ ድሬደዋ የማጏጏዣ ክፍያ £5540 እንዲሁም አገር ቤት ለምትገኘው የአዜብ ልጅ ( ኦፊሺያል ተወካይ)£1000 ወጪ ተደርጏ ተልኳል:: በቀጣይም ቀሪው £4029.96 ለመላክ ዝግጅት አድርገናል::
በመጨረሻ ከሩቅም ከቅርብም የእህታችን አዜብን ህልፈት ሰምታችሁ ሞተ እረፍቷ በሀገሯ እንዲፈፀም ለተባበራችሁ ሁሉ በግሬተር ማንቸስተር የኢትዬጵያ ኮሚዬኒቲ ስም ልባዊ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ
ከሰላምታ ጋር
ታምሩ ሰይፉ
በግሬተር ማንቸስተር የኢትዬጵያ ኮሚዬኒቲ
ሊቀ መንበር